ኬንያውያን በሰላማዊ መንገድ ድምጻቸውን እንዲሠጡ ፕሬዚዳንት ኬንያታ ጥሪ አቀረቡ

በኬንያ ለሁለተኛ  ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘዉ ምርጫ ላይ   የሚወዳደሩት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ድምፅ የሚሰጡ ዜጎች  ስላማዊ መንገድ እንዲሰጡና ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንድጠናቀቅ የሀገሪቱ ህዝቦች  የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ በበኩላቸው  ድጋፊዎቻቸው በምርጫው እንዳይሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ባለፈው ነሀሴ   በኬንያ  የነበረውን ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ቢያሽንፉም ራይላ ኦዲንጋ ለሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት  ፍርድ ቤቱ የምርጫው አካሄድ  መዛባት ታይቶበታል በሚል ውጤቱን  መሰረዝ ዳግም ምርጫ እንዲካሄድ ዉሳኔ ማስተላለፍ  ይታወሳል፡፡

ዛሬ እየተካሄደ ባለው ዳግም ምርጫ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ሆነው መራጮችን እያስተናገዱ ነው ነገር ግን የድምፅ ሰጪዎች ቁጥር ቀደም ሲል ከተደረገው ምርጫ አንፃር  ሲታይ ዝቅተኛ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ከዚህ ባልፈም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የፀጥታ ጥበቃ ኃይሎች የመራጮችን እና የምርጫ ጣቢያዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በመላው ሃገሪቱ ተሰማርተዋል መባሉን ቢቢሲ በዘገባዉ አስፍሯል፡፡

ዜጎች ለምርጫ ከመውጣታቸው አንድ ቀን በፊት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ  ባስተላለፉት መልዕክት የቀደሙ አባቶቻቸው የመምረጥ እድል እንዲያገኙ ከፍተኛ መስዋትነት መክፈላቸውን አስታውሰው  ይህ እድል በመስዋትነት የተገኘ በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም ይኖርባችዋል  በማለት  ዜጎች ድምፅ እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ አሸንፈዋል ብሎ አውጆ እንደነበር እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ደግሞ የቀረበለትን ክስ በመመርመር  የምርጫውን ውጤት ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል በዚህም ምክንያት በኮሚሽኑ ላይ ከፍተኛ ወቀሳዎች እና ጥቃቶች ሲፈፀሙ ቆይቷል።

ባሳለፈነው ሳምንት የምርጫ ኮሚሽኑ ከፍተኛ ኃላፊ የግድያ ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል የደረሰባቸውን ማስፈራሪያ ተከትሎም ኃላፊው  ወደ አሜሪካ ሸሽተዉ መሄዳቸዉ ይታወቃል፡፡

ከመጀመሪያው ምርጫ  ጀምሮ እስካሁን  ድረስ ባሉት  ሦስት ወራት ውስጥ ከምርጫ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ ግጭቶች ከሰባ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፍን የቢቢሲ ዘገባ ገልጾ  የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ የድጋሚ ምርጫው ቀነ ቀጠሮው ወደፊት እንዲሆንና መምርጫዉም ወደፊት እንዲካሄድ   ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሲጠይቁ መቆየታቸዉ ይታወቃል ነገር ግን የፍርድቤቱን ዳኞች ሳይሟሉ በመቅረታቸው ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሳይሰጥ ቀርቷል።

ከነሐሴው ምርጫ በኋላ ውዝግቡ ወደፍርድ ቤት ሄዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ ዴቪድ ማራጋ  ምርጫው በህገመንግሥቱ መሰረት አልተካሄደም ስለዚህም የምርጫው ውጤት  ልክ ያልሆነ እና  ዋጋ ቢስ ነው በማለት ውድቅ አድረገውታል። ዋና ዳኛው እንደተናገሩት ክሆነ  ከስድስቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች አራቱ የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን ሲያስተላልፍ መዛባት ተፈፅሟል 

ከዚህ  በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የምርጫው ውጤት  ግልፅ ያልነበረ እንደነበርና ሊረጋገጥም ያልቸቻለ ነው ብለዉ ነበር፡፡

ራይላ ኦዲንጋ የምርጫ ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት የፈፀመውን አይነት ስህተት እንዳይደገም ምንም አይነት ማሻሻያ አላደረገም ብለው ቢከሱም ኮሚሽኑ ይህን ክስ ውድቅ አድርጓል፡፡

ጥምር የፖለቲካ ፓርቲያቸው ምርጫው ላይ የሚሳተፈው የምርጫ ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ማሻሻያ ሲያደርግ እንደሆነ ቀድመው አሳውቀውም ነበር።

ኦዲንጋ ዛሬ እየተካሄደ ያለውን ምርጫ ለማጨናገፍ ግዙፍ ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚጠሩ አሳውቀውል በዚህም አስከፊ ግጭት እንዳይከሰት ደጋፊዎቻቸው በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ እንዳይገኙ ጠይቀዋል ሲል ቢቢሲ ዘገባውን አጠናቅሯል፡፡