ኡጋንዳ 5ሺህ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ልትልክ መሆኑን አስታወቀች

የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሬ ሙሴቤኒ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ሰር በሶማሊያ ለሚካሄደው  የሰላም  ማስከበር ተልዕኮ (አሚሶም) የሚውል  ተጨማሪ 5000 ወታደሮችን እንደምትልክ ገልፀዋል።

በአፍሪካ ህብረት በአሚሶም ጥላ ስር በሶማሊያ ከተሰማሩ ሰላም አስከባሪዎች ስድስት ሺህ ወታደሮች ያህል  የሰላም አስከባሪ ኃይልን  በማሠማራት  ኡጋንዳ ቀዳሚውን  ሥፍራ ይዛለች ፡፡

ሆኖም የገንዘብ ድጋፍ እጥረትና የወታደሮች ቁጥር እንዲቀንስ መደረጉ አልሻባብን ከሶማሊያ ወታደሮች ጋር የመፋለም ሂደት አዳክሞታል፡፡

ኒዎርክ በሚፈኘዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ በተደረገዉ ስብሰባ ሚስተር ዳላልድ ያማሞቶ ፕሬዚዳንት ሙሴቤኒ ያስደመጡትን መግለጫ በተመለከተ ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡

ሆኖም ግን ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  አሜሪካ   ለአፍሪካ  ሰላም ማስከበር ኃይል የምታደርገውን ድጋፍ  ትልቅ ግምት የሚሠጡት መሆኑን በንግግራቸው አስረድተዋል፡፡

ፕሬዚደንት  ሙሴቬኒ እንደተናገሩት ሶማሊያ በቅርቡ በአልሻባብ የደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ አልሻባብን መመከት የሚያስችል ተጨማሪ ወታደር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡  አስቀድሞ ነፃ ወጥተው የነበሩ  አካባቢዎች  አልሻባብ በፍጥነት እየተመለሰባቸው መሆኑን ተከትሎ የሰላም አስከባሪዎችን ቁጥር መጨመር አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪ 5ሺ ወታደሮችን በማሰማራት መሣሪያዎችንና ለሰላም ማስከበር ተልዕኮው የሚያግዙ  መሣሪያዎችን  ኡጋንዳ ትልካለች ብለዋል፡፡  አሚሶም  አልሸባብ  ወደ መሸገበት አካባቢ ዘልቆ  በመግባት ጽንፈኛዉን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት አለበትም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በቅረቡ በሞቃዲሾ በተሸከርካሪ በተጠመደ ቦንብ ከ300 በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን በርካቶች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ኢትዮጵያም ጽነፈኛዉ የአልሻባብ ኃይል ከምስራቅ አፍሪካ እንዲወገድ በሶማሊያ የሰላም አስከባሪ ኃይልን ማሠማራቷ ይታወቃል፡፡( ምንጭ:የኦል አፍሪካን ዶት ኮም)