የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ እንቢተኛ የሆኑ ሁለት ባለሥልጣናትን ከኃላፊነት አነሱ

የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ለመሠረተ ልማት ያወጡትን በጀት ለማሳወቅ እንቢተኛ የሆኑ ሁለት የአገሪቱ ባለስልጣናት ከሥራ ኃላፊነት አነሱ ፡፡

ኃላፊዎቹ በሚያስተዳድሯቸው አከባቢዎች ለመንገድ ግምባታ ምን ያህል ገንዘብ ፈሰስ እንዳደረጉ ማሳወቅ የነበረባቸውን ግዜ መተላለፋቸው በፕሬዝዳንቱ  ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ አድርጓቸዋል፡፡                              

ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ለህብረተሰብ ጥቅም ቅድሚያ መሥጠታቸው እና በመሠረተ ልማት ማስፋፊያ ለታንዛኒያ ጥሩ ልምድ ማሳየታቸው ሶስት ዓመት ባልሞላው የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው በግንባታ መኪናው ቡልዶዘር ቅጽል ስም ወጥቶላቸዋል፡፡

ለማህበረሰብ ልማት ሲሉ ለወጠኑት የለውጥ መንገድ በሺ የሚቆጠሩ ታታሪ ሠራተኞችን በማሠማራት በመንግስት የማስፈጸም አቅም ማነስ እና ሙስና ላይ በሁለት አመት ውስጥ በርካቶች የመሰከሩለት ውጤት አስመዝግበዋል ይላል የሮይተርስ ዘገባ፡፡

ከፕሬዝዳንት ቢሮ የወጣው መግለጫ ኃላፊዎቹ የተባረሩት ባለስልጣናት  ከፕሬዝዳንቱ የደረሳቸውን ማሰጠንቀቂያ ችላ ማለታቸው እና ለመንገድ ግንባታው ያወጡትን በጀት በጊዜው ይህን ያህል ነው ማለት  ተስኗቸው ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ለ20 አመታት ያህል የማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ማገልገላቸው እያንዳንዷ መሠረተ ልማት ግምባታ ልትፈጅ የምትችለውን ገንዘብ ያላስረጂ ማወቃቸው ለሙሰኞች አልተመቹም ተብሏል፡፡

እኤአ በ2015 ላይ ሥልጣን የያዙት የታንዛንያው ፕሬዝዳንት በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ሲያገለግሉ የነበሩ 12 ሺህ የመንግስት ሠራተኞችን አታስፈልጉም ብለው ማባረራቸው ከለውጥ ጉዞ ትግበራቸው የሚካተት ሆኗል ።

የአብዛኛው ዜጋ ጥቅም በጥቂቶች እጅ እንዲገባ ፈቃዴ አይደለም ያሉት ማጉፉሊ ለብልሹ አሠራሮች መክሰም እንቅልፍ የለኝም በማለት ከቃለ ማሃላቸው ማግስት  የጀመረው ታታሪነታቸው ከዛሬው ወጫቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ ያልሆኑ ባለሥልጣናት ማባረር ላይ ደርሷል፡፡

ከታክስ ማጭበርበር እና የሀብት ምዝበራ ጋር ተያይዞ በሰሩት ምግባር ከበርካታ የምዕራባዊያን ግብረሰናይ ድርጅቶች የጀግና ሽልማት አግኝተዋል፡፡ በጎን ፕሬዝዳንቱ አድራጊ ፈላጭነታቸው በዛ የሚሉ ቢበራከቱም መንግስቴ ለዲሞክራሲ ቦታ ያለው ነው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ( ምንጭ: የሮይተርስ)