የዙምባብዌ መከላከያ ሠራዊት መላ ዚምባብዌን በቁጥጥር ሥር አዋለ

የዚምባብዌ  መከላከያ ሠራዊት በአሁኑ ወቅት መላ አገሪቱን ተቆጣጣሮ እንደሚገኝ ተመለከተ ።

የሀገሪቱ ህግ አውጪዎች የመከላከያ ኃይሉ ድርጊት ህገ መንግስቱን የጠበቀ ነው ብለዋል፡፡

እኤአ ከ1980 ጀምሮ ዚንባብዌን ሲመሩ የቆዩትን የ93 ዓመቱን አዛውንት ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ትናንት በቁጥጥሩ ሥር ያዋለው የሀገሪቱ መከላከያ ኃይል ቀጣይ እርምጃ ምን ይሆን የሚለው ጥያቄ ዚምባብዌያውያንን በጉጉት እንዲጠባበቁ አድርጓል፡፡

ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ደህንነታቸው ተጠብቆ በቤታቸው ቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ከሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር የወጣ መረጃ ያስረዳል፡፡ ሙጋቤን ተክተዉ ቀጣይ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከመጋረጃ በስተጀርባ የነበሩት የዚምባብዌ ቀዳማዊት እመቤት ግሬስ ሙጋቤ ወደ ናሚቢያ ስለመሰደዳቸው መረጃዎች ቢጠቁሙም እስካሁን ባለው ሁኔታ ግን መረጃውን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡

የወታደራዊ እርምጃውም ከቀናት በፊት ከፕሬዝዳንት ሙጋቤ ቀጥሎ በትረ-ስልጣኑን ለመያዝ ከሚስ ግሬስ ሙጋቤ ጋር በብርቱ ይፎካከራሉ ተብለው የተጠበቁትን የቀድሞ የዚምባብዌ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ማናንጋዋ ከስልጣን መባረራቸውን ተከትሎ የተወሰደ ነዉ፡፡ ሚስተር ማናንጋዋ እንኳን አሁን የት እንደሚገኙ በውል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡

ሙጋቤ ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲያቸውን በመወከል ላለፉት 37 ዓመታት ዝምባብዌን በፕሬዝዳንትነት መርተዋል፡፡ በቀዳማዊቷ እመቤት ግሬስ ሙጋቤ እና የቀድሞ የሙጋቤ ወዳጅ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ማናንጋዋ መሃል የተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻ አንጋፋውን የሀገሩቱን ገዢ የፖሊቲካ ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍን ለሁለት ተከፈሏል፡፡

ማስረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ከመከላከያ ኃይሉ ጊፊቶች እየተበራከቱ ከመምጣቱ አንድ ቀን አስቀድሞ አንድ የግሬስ ሙጋቤ የቅርብ ወዳጅ በሀገሪቱ ወታደራዊ መሪ ላይ አቅርበው ለነበሩት ወቀሳ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ሀገራት ማህበረሰብ ልማት የተሰኘዉ የአከባቢዉ ጥምረት ዛሬ ለአስቸኳይ ውይይት ቦትስዋና ላይ ስብሰባ ጠርቷል፡፡ የዚምባብዌ የተቃዋሚ ፖሊቲካ ድሪጅት መሪ ቴንዳይ ቢቲ የሽግግር ግብረ ኃይል በሀገሪቱ እንዲቋቋም ፊላጎታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡   

ቢቢሲ እንደዘገበው ህዝቡ ሁሉ ግራ በመጋባት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ አጋጣሚው ዚምባቢዌን ወደ ዴሞኪራሲ የሚያመራት ነው የሚሉ እንዳሉ ሀገሪቱ ወደ ባሴ ግጭት ላለ ማቅናቷ እርግጠኛ ያልሆኑ ዜጎችም ቁጥር በርካታ ነው፡፡ ሱቆች እና የንግድ ተቋማት ግን የወትሮ ስራቸውን ቀጥሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙጋቤም ደህንነታቸው ተጠብቀዉ በቤት ዉስጥ መሆናቸዉ እና ለህይወታቸዉ እንደማያሰጋ ያትታል ዘገባዉ፡፡ ይልቅ ወታደሮቹ እና በርካታ የሲቪል ዜጎች በሀገሪቱ የተፈጠረ መፈንቅለ መንግስት አለመኖሩን ለዓለም ህዝብ ለማስረዳት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸዉ፡፡

ነገር ግን የ93 ዓመቱ አዛዉን ሙጋቤ በነዚህ 2 ቀናት ዉስጥ ያሉበትን ሁኔታ አስመልክቶ መቼ ቃል ይሰጣሉ? የባለቤታቸዉ እና ቤተሰቦቻቸዉ ሁኔታስ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? በወታደራዊ ሀይሉ የተወሰደው እርሚጃ እስከመቼ ይቆያል የሚለው ጥያቄ መቀጠሉ በዚምባብዌ ወታደራዊ ድራማ ይመስላል፡፡

እስካሁንም ግን በሀገሪቱ የተሰማ ረብሻ የለም፡፡ ያለ ወትሮዉ የሀራሬ ጎዳናዎች ፀጥታ ሰፍኖባቸዋል፡፡ ህዝቡ ግን የእለት ስራውን ተረጋግቶ ቀጥሏል፡፡

ትናንት የሀገሪቱን ቁልፍ ቦታዎችን ጨምሮ የሀገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ዜድ ቢሲን የተቆጣተረው የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል በፕሬዝዳንቱ ዙሪያ ያሉትን የሙስና ቅሌቶች አጣራለሁ ብሏል፡፡ 

ሜጀር ጀነራል ሲቡሲሶ ሞዮ ወታደራዊ ኃይሉ መንግስትን የመገልበጥ ሃሳብ የለውም ብሏል፡፡ የፕሬዝዳንቱ እና ቤተሰቦቻቸዉ ደህንነትም የተጠበቀ ነው ሲል መተማመኛ ሰጥቷል፡፡ ተልዕኮአቸውን እንደጨረሱም ነገሮች ወደተለመደው ሁኔታ እንደሚመለስ ቃል ገብተዋል፡፡

ባሰለፍነዉ ሰኞ የሀገሪቱ የጦር መሪ ኮኒስታንቲኖ ቺዌንጋ በሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍ መሃል የተፈጠረዉ መከፋፈል የማይፈታ ከሆነ ወታደራዊ ኃይሉ እርምጃ እንደሚወስድ ዝተዉ ነበር፡፡

ጄነራል ቺዌንጋ የ ሚስተር ማናንጋዋ የቅርብ ወዳጅ ሲሆኑ በ1970ዎቹ የአናሳው የነጮች አገዛዝ ለማብቃት በተደረገው ትግልም አብሮ የታገሉ ናቸው፡፡

የዛኑ ፓርቲ የወጣቶች ሊግ መሪ እና የሙጋቤ ቅርብ ሰው ኩድዛይ ቺፓንግዋ ወጣት እንደመሆናችን ስህተቶችን ልንፈጥር እንችላለን በሚል ለወታደራዊ ኃይሉ ድጋፋቸውን በመግለፅ ለጄነራል ቺዌንጋ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ወታደራዊ ኃይሉ ሀገሪቱን ከመቆጣጠሩ አንድ ቀን አስቀድመዉ ለሙጋቤ ስንል ህይወታችን እንሰጣለን ማለታቸው አይዘነጋም፡፡

ዚምባብዌያውያን በተለይ የሮበርት ሙጋቤን አገዛዝ የሚኮኒኑ ዜጎች ጊዜዉ በጋራ ቆመን የተሸለች ዚምባብዌ ለመፍጠር ህብረት የሚያስፈልገን ወሳኙ ጊዜ አሁን ነዉ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡

የዚምባብዌ ህግ አዉጪ ተቋም ዲርጊቱ ህገ-መንግስታዊ ነዉ በመለት ሃሳቡን ሰቷል፡፡ የፓርላማ የግል አባል የሆኑት ቴምባ ሚሊስዋ ወታደራዊ ሀይሉ በሙጋቤዋ ቀዳማዊት እመቤት የተፈጠረዉን የሀገር መበጣበጥ ለመቆጣጠር የተወሰደ በማለት ነዉ የገለፁት፡፡

አጋጣሚዉ በተለይ በሀገር ዉስጥ ላሉ የዚምባብዌ ዜጎች መልካም ዜና ነዉ ሲሉ ለአልጀዝራ ገልፀዋል ሚሊስዋ፡፡ የዚምባብዌ ህዝብ ሮቤርት ሙጋቤን እንጂ ግሬስ ሙጋቤን አይደለም በፕሬዝዳንትነት የመረጠዉ፡፡

ወታደራዊ ኃይሉ ህግን የማስከበር ስራን እየሰራ ነው ብሏል፡፡ የዚምባብዌ የጦር አርበኞች ማህበር ዋና ፀሃፊ ቪክቶር ማቴማንዳ ሙጋቤ ከፕሬዝዳንትነቱም ሆነ የዛኑ ፓርቱ  ኃላፊነታቸዉ መልቀቅ አለባቸዉ የሚል ጥሪያቸዉን አቅርቧል፡፡

የአልጀዚራዉ ሃሩ ሙታሳ ሁኔዉን ሲገልፅ እኔ የተወለድኩኝ ከእንግሊዝ ነፃ ከወጣን በኋላ ነዉ፡፡  እንደ አንድ የዚምባቢዌ ዜጋ የዚህ አይነቱን ነፃ አየር ግን ተንፍሼ አላዉቅም ብሏል፡፡