ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከዛኑ ፒኤፍ መሪነት ወረዱ

ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከፓርቲያቸው ዛኑ ፒ ኤፍ መሪነት ወረዱ፡፡

ከሥልጣን ተባረው ከዙምባብዌ ውጭ የተሰደዱት ምክትል ፕሬዚዳንት ኢመርሰን ምናንግዋ የፓርቲውን መሪነት እንዲረከቡ መደረጉም እየተነገረ ነው፡፡

ባሳለፍነው ረቡዕ የዙምባብዌ መከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጨምሮ ቁልፍ ተቋማትን መቆጣጠሩንና ፕሬዝዳንት ሙጋቤም በመኖሪያ ቤታቸው በሰላም እንዲቆዩ መደረጋቸውን ካሳወቀ በኋላ በሀገሪቱ ምን እየተካሄደ ነው የሚለው አለምን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡

በመጨረሻ የዙምባብዌ ገዢ ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍ  ለአራት አሥርት አመታት ለሚጠጋ ጊዜ አገሪቱን የመሩትን ሙጋቤን ከፓርቲው ፕሬዝዳንትነት ያነሳበትን ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ሙጋቤ ከፓርቲው ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንትነታቸውም በፈቃዳቸው ሥልጣን እንዲለቁ ፓርቲው ጥሪውን አስተላልፎላቸዋል፡፡

ሙጋቤ ሀሳቡን ያለመቀበል ጠንካራ አዝማሚያ እንዳላቸው እየተነገረ ነው፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከ24 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በፈቃዳቸው ሥልጣን የማያስረክቡ ከሆነ በህግ ፊት ውሳኔ እንዲሰጥበት ፓርቲው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ለመውሰድ ማቀዱም ተሰምቷል፡፡

ሙጋቤ ለሥልጣን ሲያመቻቹዋቸው ነበር የተባሉት ባለቤታቸው ወይዘሮ ግሬስ ሙጋቤ ከፓርቲው አባልነት ሙሉ በሙሉ እንዲባበረሩ ተደርጓል፡፡ ሌሎች ከሙጋቤ ጋር ቅርበት እንዳላቸው የተጠረጠሩ አባላትም ከፓርቲው ተሰናብተዋል፡፡

 ከውሳኔው በፊት የሙጋቤን አስተዳደር የሚቃወሙ እና የተባረሩትን ምክትል ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንግዋን የሚደግፉ እጅግ በርካታ የሀገሪቱ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ መታየታቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡