ሶማሊላንድ ሙሳ ቢሂ አብዲን ፕሬዚደንት አድርጋ መረጠች

ሶማሊላንድ የገዢ ፓርቲውን እጩ የሆኑንት ሙሳ ቢሂ አብዲን አዲሱ ፕሬዝዳንት አድርጋ መረጠች ።

በሶማሊ ላንድ ከሳምንት በፊት በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሶስት እጩዎች አህመድ መሐመድ ሲላንዮን ለመተካት ተወደድረው እንደነበር ይታወሳል 

የቆጠራውን መጠናቀቅ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ተወካይ ሙሳ ቢሂ አብዲ ማሸነፋቸውን በምርጫ ኮሚሽን በኩል ይፋ ሆኗል፡፡

ሙሳ ቢሂ አብዲ ከገዢው ፓርቲ የሶማሊላንድ አዲሱ ፕሬዝዳንት መሆነናቸዉን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡

ምንም እንኳን አለም አቀፍ እዉቅናን ማግኘት ባትችልም ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሶማሊላንድ በንግድ መዳረሻነቷ የብዙዎችን ቀልብ እየሳበች ትገኛለች፡፡

እንደ አዉሮፓዉያኑ ዘመን በ1991 ከሶማልያ መግንጠሏን ተከትሎ አንፃራዊ ሰላም እንደሰፈነባት የተለያዩ ምንጮች ያትታሉ፡፡ አራት ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሀገሪቱ አለም አቀፍ እዉቅና ማግኘት ባትችልም በቀጠናዉ ዋነኛ የኢንቨስትመንት መደረሻ መሆን ችላለች፡፡

በድርቅ ምክንያት ከተያዘለት ጊዜ ለስምንት ወራት ዘግይቶ በተደረገው ምርጫ ሙሳ ቢሂ አብዲ 55 በመቶ የምርጫ ድምፅ አግኝተዋል፡፡ በምርጫዉ ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ የነበሩት ተቀናቃኙ አብድረሀማን መሐመድ ኢሮ 41 በመቶ ድምፅ ማግኘት ችለዋል፡፡

ከአንድ ሳምንት አስቀድሞ በተከናወነው ምርጫ በተደረገው ክርክር ተመራጩ አብዲ የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ መጎልበትና ወጣቶችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቆች በሄራዊ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ፕሮግራም ይዘው መቅርባቸው የሚታወስ ነዉ፡፡

የዋዳኒ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አብዱርሃማን መሐመድ ኢሮ እስካሁን ምንም አይነት አስተያየት ያልሠጡ ሲሆን የገዢውን ፓርቲ ተመራጭ ማሸነፍ አስመልክቶ ከተቃዋሚዎች የወጣ ማረጋገጫ አለመኖሩ ታውቋል፡፡

ፕሬዝዳንታዊ ምርጫው አስቀድሞ በ2015 መከናወን የነበረበት ሲሆን በሀገሪቱ በተከሰተ ድርቅና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ዘንድሮ ከተያዘለት ስንት ወር ዘግይቶ ለመከናወን በቅቷል፡፡

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያና ጅቡቲ ካላት ጠንካራ ግንኙነት በተጨማሪ በቀጠናው ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኑኟን ተንታኞች ያነሳሉ፡፡

በዚህ አመት መጀመሪያ የሀገሪቱ መንግስት ከተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ወታደራዊ ተቋም በበርበራ ወደብ ለመገንባት መስማማታቸዉ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ከሶማሊላንድ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርስ ግንባታ ለመከናወን ያቀደ ሲሆን በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር እንደሚሰራም ታዉቋል፡፡ (ምንጭ:ሮይተርስ)