በናይጄሪያ የሽብር ጥቃት 50 ሰዎች ተገደሉ

በምስራቃዊ የናይጄሪያ ግዛት በሆነችው  የአዳማዋ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 50 ሰዎች መገደላቸው  ተገለጸ ።

አንድ  ናይጄሪያዊ  በአዳማዋ ግዛት ሙቢ ከተማ  በሚገኝ  መስኪድ  የቦንብ ጥቃት በማድረሱ 50 የሚሆኑ  በመስኪዱ የሚገኙ ሰዎች  ተገድለዋል ።    

አቡበከር ሱሌ  የተባለ  አይን ምስክር  ለኤፍፒ የዜና ወኪል  እንደተናገረው  የቦንብ ጥቃቱን  የፈጸመው ግለሰብ በመስኪዱ  ውስጥ  ጸሉት ከሚያደርጉት  ሰዎች  ጋር አብሮ እንደነበር ጠቁሟል ።  

ከሽብር ጥቃቱ ጀርባ  ማን እንዳለ  እስካሁን   የተገለጸ  ነገር  የለም። ሆኖም  እስልምና አክራሪ ቡድን የሆነው ቦኮሃራም  በአብዛኛው  በሰሜን ናይጄሪያ  ህዝብ  በሚበዛባቸው  ሥፍራዎች ጥቃት የሚሰነዝር በመሆኑ  የጥቃቱ  ቁጥር አንድ ተጠርጣሪ መሆኑ እየተገለጸ ይገኛል  ።

የቢቢሲው ኢሻቅ ካህሊድ እንደሚገልጸው የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች  በቅርቡ በሰሜን ምስራቅ አካባቢ  በቁጥጥር  ሥር ያዋሏቸው ይዞታዎች   በናይጄሪያ  ወታደሮች ከተነጠቁ  በኋላ ሁለት  ሴት አጥፍቶ ጠፊዎች  በገበያ አካባቢ በፈጸሙት ጥቃት   45 ሰዎች  መግደላቸው  ይታወሳል ።( ምንጭ: ቢቢሲ)