ሪክ ማቻርና ሳልቫ ኪር ከፊል ስምምነት ላይ ደርሱ

 ሪክ ማቻርና ሳልቫኪር  ከፊል ስምምነት  ላይ  መድረሳቸው  ተገለጸ ።

 

ማቻርና ኪር ስምምነት የደረሱባቸው ነጥቦች ግን ለጊዜው አልተገለጹም።

 

 የሁለቱ ተፋላሚዎች የስምምነት መልካም ዜና የተሰማው ከካርቱም ሲሆን የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልማዲሪ ሙሐመድ አሕመድ «በተወሰኑ ጉዳዮች» ላይ ብቻ ስምምነት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።

 

በደቡቡ ሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለዋል።

4 ሚሊዮን የማያንሱ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

 

ይህ የሰላም ስምምነት በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የቀረበ ሲሆን በቅርቡ አዲስ አበባ በተደረገ የአባል አገራት መሪዎች ስብሰባ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቶ ነበር።

 

ሁለቱ ተፋላሚ መሪዎች ባለፈው ሳምንት የፊት ለፊት ንግግር ሲጀምሩ በአካል ለመገናኘት ከሁለት ዓመታት በኋላ የመጀመርያቸው ነበር።