በሱዳን የሚደረግ ለውጥ የሀገሪቱን ህገመንግስት ያከበረ ሊሆን ይገባል – የአፍሪካ ህብረት

የአፍሪካ ህብረት የሰላም ደህንነት ምክር ቤት በሱዳን የሚደረግ ማንኛውም ለውጥ የሀገሪቱን ህገመንግስት ያከበረ ሊሆን ይገባል አለ፡፡

ምክር ቤቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣን መያዙንና ለሁለት ዓመት እቆያለሁ ማለቱን አውግዟል ::

ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣኑን ለሲቪል በመስጠት ሽግግሩን ሰላማዊ እንዲያደርግም አሳስቧል::

የሱዳን ህዝብ የለውጥ ፍላጎትን እንደሚያከብር የገለፀው የአፍሪካ ህብረት የሰላም ደህንነት ምክር ቤት ሂደቱ ግን ህግን ያከበረ ሊሆን ይገባል ብሏል::

የአፍሪካ ህብረትም ሆነ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርብ በመከታተል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቋል::