ድርጅቱ በሶማሊያና ሱዳን የአሚሶም ልዩ ኃይል የቁሳቁስ ድጋፍ ሊያደርግ ነው  

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሊያ እና በሱዳን ላለው የአሚሶም ልዩ ኃይል የገንዘብና  የቁሳቁስ ድጋፍ ሊያደርግ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ሥራ የሚሆን ድጋፍ ለማድረግ ተስማምቷል፡፡

በዋናነትም በሶማሊያ እና ሱዳን ላለው የፀጥታው ኃይል የሚውል ነው ተብሏል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ኒኪ ሀሊ እንዳሉት ከሆነ የአፍሪካ ህብረት በሰላም ማስከበር የሚሠራቸው ሥራዎች በርካታ እና እጅጉን አጥጋቢ  ነው።

የተባበሩት መንገስታት ድርጅት ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር መሥራቱ እና ድጋፍ ማድረጉ ትርፉ ለሁላችንም ነው ብለዋል ፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሽብርተኝነትን እና አክራሪነትን ለማጥፋት ያቀደናቸውን እቅዶች በተፋጠነ ደረጃ ለማስኬድ ያስችላል ነው ያሉት፡፡

የአፍሪካ ህብረት በተለይም ሽብርተኝነትን እና አክራሪነትን ለማጥፋት የሚወስዳቸው እርምጃዎች እና የሚያደርጋቸው ቅንጅቶች አመርቂ በመሆናቸው ከዚህ በበለጠ መራመድ እንዲችል የፋይናንስ ድጋፉ አስፈላጊ ነው፡፡

ሃሊ አክለውም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ለአሚሶም የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሊያ እና ሱዳን ላለው የሰላም አስከባሪ ኃይል ድጋፍ ከመሥጠቱም ባለፈ በአሚሶም ኩለክ ለእየሀገራቱ የወታደር ኃይል የሥልጠና የግብዓት እና የፋናንስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

አሁን የሚደረገው ድጋፍ በዋናነት በሶማሊያ ላለው የአሚሶም ኃይል እና በሱዳን ላለው የፀጥታው ኃይል የሚውል ነው ተብሏል፡፡ እኤአ  እስከ 2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ህብረት ከ8 ሺህ በላይ ሰላም አስከባሪ እና ከ15 ሺህ በላይ የተለያዩ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትን ልኳል፡፡ 

የተባበሩት መንግስታት 80 ከመቶ የሚሆነው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሚያካሄደው በአፍሪካ ሲሆን ይህንም ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመቀናጀት ይሠራል፡፡  

ከመካከለኛው አፍሪካም በሪፐብሊክ ጎንጎ ዳርፉር በደቡብ ሱዳን በማሊ እና ሶማሊያ ከፍተኛ የሆነ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ  ልዩ ኃይል ያለባቸው ሀገራት ናቸው፡፡

በአፍሪካ በአሸባሪዎች  የደረሰውን ጥፋት አለሻባብ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን እንዳቀነባበረው  መረጃዎች  አመላክተዋል፡፡

በሶማሊያ መሽጎ የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን ሲያደርስ የቆየው አልሻባብ የተሰኘው የአሸባሪ ቡድን እኤአ ከ2012 – 2015 ባለው ጊዜ ብቻ በርካታ ህይወት በማጥፋት በቀዳሚነት ሲጠቀስ በናይጄሪያ የመሸገው ቦካሃራም ደግሞ በቀጣይነት ይጠቀሳል፡፡

ኒው ፊገር ፍሮም ዘ አርምድ  ኮንፍሊክት ሎኬሽን  ኤንድ ኢቨንት  ዳታ ፕሮጀክት  እና የ አፍሪካ ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ሰቱደንት የተሰኙት ተቋማት በጋራ ባወጡት ጥናት አልሻባብ በአፍሪካ በተለይም  በሶማሊያ ለጠፋው  4,281  ነፍስ ሀላፊነቱን ሲውስድ  በኮሃራም በበኩሉ 3,499 ሰዎች ነፍስ ሃላፊነቱን ወስዷል፡፡

በዚሁ ጥናት መሰረት በ2016 ብቻ ኣይ ኤስ 2,350 ሰዎች ነፍስ መጥፋት ሀላፊነቱን ውስዷል፡፡

በዋናነት አለሻባብ እና አልቃይዳ በመቀናጀት  በኬንያ ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ እና በዌስትጌት የገበያ ማዕከል ያደረሱት ጥፋት እጅጉን አሰከፊ እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡

ጥናቱ እንዳለው ከሆነ ጥፋቱ ከዚህም ይበልጥ እነደነበር ጠቅሶ በተለይም የኢትዮጵያ  ሰላም አስከባሪ ኃይል ጥፋቱን ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ ድርሻውን ተውጥቷል ብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈ የሶማልያን ጦር ከመደገፍ እና የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመሥጠት ረገድ  በአሚሶም በኩል ኬንያና እና ኢትዮጵያ የተወጡት ሚና የጎላ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ፋርማጆ ተቋማ ያሏቸውን ፓርቲዎች እና ጥቃት አድራሾችን  ወደ ድርደር  መድረክ እንዲመጡ መጥራታቸው ለጥቃቱ መቀነስ እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡

በሌላ በኩል በኮሃራም ትኩረቱን እራሱን ለማደርጀት እና አቅሙን  ለማበልጸግ ወደ ሰሜናዊ ቻድ በማድረጉ በተወሰነም ደረጃ ጥቃቱ ሊቀንስ ችሏል፡፡ እስከ አሁን ባለው መረጃ መሰረት አልሻባብ 6 ቢሊዬን ዶላር እንደሚያንቀሳቅስ እና የገቢ ምንጩን በማሳደግ ላይ እንዳለም መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡

በአፍሪካ  በአሸባሪዎች የደረሰውን ጥፋት አለሻባብ የተሰኘው አሸባሪ ቡድን እንዳቀነባበረው  መረጀዎች  አመላክተዋል፡፡