የቻይና መንግሥት በድርቅ ለተጋለጡ ሶማሊያውያን የ1 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ሠጠ

የቻይና መንግስት በድርቅ ለሚሰቃዩና ለተፈናቀሉ የሶማሊያ የህብረተሰብ ክፍሎች በእርዳታ የሚሰጥ የ 1 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠች።

ጎረቤት ሃገር ሶማሊያ በየጊዜው የሚያጋጥማት የድርቅና የረሃብ ችግር ለመላቀቅ የአለም ሃገራት እርዳታ ስትሻ ቆታለች፡፡

አሁን ካለችበት የድህነት አዘቅት ለመውጣትና ገፅታዋን ለመቀየርም እየጣረች እንደሆነ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሲዘግቡ እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡ አሁንም ግን ከድርቅ መላቀቅ አልቻለችም፡፡

ቻይና በሶማሊያ ለተፈናቀሉ እና ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኩል የሚሰጥ የ 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገረገች፡፡

ቻይና ወደ አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) የላከችው ገንዘብ ኤጀንሲው የስደት ቀውሱን እንዲያስተካክል እና በሶማሊያ ውስጥ ለሚገኙ ስደተኞች መጠለያ እንዲሆን ይረዳል፡፡ 

በሶማሊያ የደረሰው ድርቅ እስካሁን ድረስ የቀጠለ ሲሆን ድርቅን ለመግታት ደግሞ ከሶማሊያ መንግስትና ከአለም አቀፍ ጋሮች ጋር ተባብረው በመስራት ላይ መሆናቸው ሽንዋ ዘግቧል፡፡

የሶማሊያ መንግስት በበኩሉ ቻይና ድርቁን ለመታደግ ላደረገችው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናውና ገልጿል፡፡

የተፈጥሮ አደጋ ቁጥጥር እና የሰብአዊ እርዳታ ሚኒስትር ዋና ፀሃፊ ሞሃመድ ሟይላም እንደተናደሩት ቻይና ለሶማሊያ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሃገራት መካከል መሪ ናት፡፡

ቻይና አሁን ባደረገችው እርዳታም ለ 2500 ቤተሰቦች ና ሞቃዲሾ የሚገኙ በረሃብ፣ በድርቅና በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ከ ግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን ነው አክለው የገለፁት፡፡

በሶማሊያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ኪን ጂያን በበኩላቸው የሃገራቸው መንግስት ሶማሊያን ለመደገፍና በሁለቱ ሃገራት ያለው ወዳጅነት ለማጎልበት በመስራት ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ቻይና በሶማሊያ የቤናዲር ሆስፒታልና የሞቃዲሾ ስቴዲየምን እንደገና ለመገንባት ከሃገሪቱ መንግስት ጋር የተስማማች ሲሆን ከዚህ በፊትም 89 ፕሮጀክቶችን በሶማሊያ አከናውናለች፡፡ ( ምንጭ: ዠንዋ)