በጅቡቲ ለሰፈሩ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ አለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት ርብርብ እያደረጉ ነው

በጅቡቲ ለሰፈሩ የተለያዩ ሃገራት ስደተኞች ተስፋ ለመሆን በርካታ አለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት ርብርብ እያደረጉ ስለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

አሊ አድህ በተባለ ስደተኛ ጣቢያ ለተጠለሉ ስደተኞች የአውሮፓ ህብረት ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ መጀመሩ ለስደተኞች ካለው ፋይዳ ጎን ለጎን ለአከባቢው ኢኮኖሚ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ተብሏል፡፡

በምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ጅቡቲ ለሚገኙ ከ27 ሺህ በላይ ስደተኞች ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የአውሮፓ ህብረት እና የአለም ምግብ ፕሮግራም በጣምራ የሰብዓዊ እርዳታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል ይላል ስለ ጅቡቲ ስደኞች የሰብአዊ እርዳታ የወጣው መረጃ ፡፡

በየወሩ የአለም ምግብ ድርጅት  ለ18 ሺህ 500 ስደተኞች በምግብ መልክ እና በገንዘብ እርዳታ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

የድርጅቱ የስራ ሀላፊዎች ቦታው ድረስ በመሄድ በጅቡቲ ላለፉት 25 አመታት በስፍራው የነበሩ ስደተኞችን ጎብኝተዋል፡፡

በአመዛኙ በረሃማ የአየር ንብረት ባለቤት የሆነችው ጅቡቲ ከአምስት ዜጎቿ ሁለቱ እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከ27 ሺህ በላይ ስደኞቸችን ከየመን እስከ ሶማሊያ ድረስ በቀጠናው ሰላም ከመጥፋቱ ጋር ተያይዞ እያስተናገደች ነው፡፡