ዢ ጂንፒንግ በ“ሲልክ ሮድ” ፕሮጄክት ውጤታማነት ተማምነዋል

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ አውሮፓንና እስያን ከሌላው የዓለም ክፍል ጋር በነፃ ንግድ የሚያስተሳስረው የቀለበትና መንገድ ቤልት ኤንድ ሮድ ፕሮጄክት ውጤታማ እንደሚሆንና በርካታ አገራትን ተጠቃሚ እንደሚያደረግ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በቤጂን ለሁለት ቀናት የቆየውን ጉባዔ መጠናቀቅ አስመለክተው ፕሬዝዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሁሉም የዓለም ክፍል ከተባበረ ፕሮጄክቱ ለምድራችን ሰላምና ብልፅና እንደሚያመጣ አስረድተዋል፡፡

ቻይና ለሁሉም ክፍት፣ ሚዛናዊ እና የበለፀገች ዓለምን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚሪነቱን ሚና እየተወጣች እንደሆነም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ፕሮጄክቱ ከስልሳ በላይ አገራት የሚኖሩ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ሕዝቦችን እንደሚያገናኝ ተጠቁሟል፡፡

የ“ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ'' ፎረም ላይ የ29 ሀገራትና መንግስታት መሪዎች፣ የ70 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች እና 100 የሚሆኑ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል፡፡

ቀጣዩ የቤልት እና ሮድ ጉባዔ በ2011 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ፕሬዝዳንቱን ጠቅሶ ሪውተርስ ዘግቧል፡፡