የብሪክስ ልማት ባንክ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በደቡብ አፍሪካ ሊፍት ነው

የአምስት ሀገራት ጥምረት የሆነው ብሪክሰ የመጀመሪያ ቅርንጫፉ የሆነውን ልማታዊ ባንኩን  በደቡብ አፍሪካ እንደሚከፍት አስታወቀ ።

ብሪክሰ የአምስት ሀገራትን የመጀመሪያ ቃል ወሰዶ ምህፃረ ቃል የተቀመጠ ነው፡፡ አገራቱም ብራዚል ፣ ሩሲያ ፣ ህንድ ፣ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡

የመጀመሪያዎቹ አባል ሀገራት ብራዚል ፣ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና የነበሩ ሲሆን አፍሪካዊቷ ሀገር ደቡብ አፍሪካ ህብረቱን የተቀላቀለችው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ነበር፡፡

ሀገራቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢንዱስትሪ እንዲሁም በአጠቃላይ ምጣኔ ሀብት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ካሉ  የአለም አገራት ውሰጥ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ አምስቱም ሀገራት የቡድን 20 አባላትም ጭምር ናቸው፡፡

ሀገራቱ በተለያየ ጊዜ በመገናኝት የጋራ የሚያደርጉቸውን አጀንዳዎች በማንሳት እና የጋራ የንግድ እንቅሰቃሴ ላይ እንዲሁም በአካባቢ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡

በተለይም በሀገራቱ መካከል በሚደረጉ የንግድ እንቅሰቃሴዎችን እንዴት ማጠናከር እንደሚገባቸው እና የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ይንቀሳቀሳሉ፡፡

ሀገራቱ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ካላቸው ሀገራት የሚጠቀሱ ሲሆን ይህንን እንዴት ወደ እድገት እንደሚቀይሩ እና ምጣኔ ሃብታቸውን እንዴት እንደሚያሳድጉ የጋራ ምክክር  ያደርጉበታል፡፡

የብሪክስ አባላት 3ነጥብ 6 ቢሊየን የአለም ህዝብን ይወክላሉ የሚወክሉ ሲሆን  የሀገራቱ አመታዊ አጠቃላይ  ምርት 16ነጥብ 6 ትሪሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም የዓለምን 22 በመቶ የሚሆነውን  የአለምን ገቢ ይሸፍናል፡፡

ይህንን አመታዊ ገቢ አሁን ካለበት ይበልጥ ለማሳደግ እና የጋራ ተጠቃሚነታቸውንም ፍታሃዊ በማድረግ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን በሁሉም መስክ ዙሪያ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ይናገራሉ፡፡  

በፋይናንስ፣ በንግድ፣ በጤና ፣በትምህርት፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣በግብርና እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ በአምሰቱም አገራት በትብብር ለመሥራት ባቀዱት መሠረት ባለፍነው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ  ጁሃንሰበርግ የመጀመሪያ የሆነውን የልማት ባንክ  በመክፈት ሥራ እንደሚጀምር ይፋ አድርዋል፡፡

ባንኩ የደቡብ አፍሪካን ብሎም የመላው አፍሪካን የመሰሠረተ ልማት እና በሁሉም ዘርፎች ዘላቂ ልማትን ለማጎልበት ጉልህ ሚና ይጫወታልም ተብሏል፡፡

ሀገራቱ ከያዙዋቸው እቅዶች ውሰጥ ከታዳሽ ኃይል የሚገኘውን የኤሌክትሪክ አቅርቦትን  የሚያጠናክሩ ፕሮጀክቶችን በደቡብ አፍሪካ በቅርብ ጊዜያት ውሰጥ ለመጀመር 180 ሚሊየን የአሚሪካ ዶላር በጀት መድበዋል፡፡( ምንጭ: ሲጂቲኤን)