ቻይና ሩሲያ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ላይ የሚያተኩር ውይይት ሊያደርጉ ነው

የብሪክስ አባላት የሆኑት ቻይናና ሩሲያ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የንግድ ትብብርና ሁሉን አቀፍ እድገት ላይ ያተኮረ ውይይት ሊያደርጉ ነው፡፡  

የ ቡድን 20 ኣባል ሃገራት የሆኑት የአምስቱ ሃገራት ማለትም የብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና ና ደቡብ አፍሪካ ናቸው፡፡ የአምስቱ ሃገራት ዋነኛ ብሄራዊ ኢኮኖሚዎች ማህበር በምህፃረ ቃል ብሪክስ ተብሎ ይጠራል፡፡

እነዚህ አምስቱ የብሪክስ አባላት በፈረንጆቹ 2015 በተደረገው ጥናት መሰረት ከ 3ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ወይም ከዓለም ህዝብ 40 ከመቶውን ይወክላሉ፡፡ አምስቱም ሃገራት በዓለም የህዝብ ብዛት ከተቀመጡ 25  ሃገራት መካከል ናቸው፡፡

ሃገራቱ አጠቃላይ ዓመታዊ የገቢ መጠናቸው 16 ነጥብ 6 ትሪሊዮን ዶላር ሲሆን አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸው ደግሞ 4 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል::

የሩሲያ አምባሳደር ኢቫኖቪች ዲኒሶቭ እንደገለጹት የብሪክስ አባላት የሆኑት ቻይናና ሩሲያ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የንግድ ትብብርና ሁሉን አቀፍ እድገት ላይ ያተኮረ ውይይት  በደቡብ ቻይና በሚደረገው የብሪክስ ስብሰባ ላይ ለመወያየት አስበዋል፡፡

 

ይህ ደግሞ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የኢኮኖሚ ትብብር ጠንካራ ተስፋዎች ያሳያሉ ተብሎ  ነው የሚጠበቀው፡፡

ቻይና በ 2016 52ነጥብ 48 ሚሊዮን ቶን የነዳጅ ዘይት ከሩሲያ በመግዛት በየዓመቱ ከነበረው መጠን ወደ 23ነጥብ 7 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ ሩሲያ የቻይና ከፍተኛዋ ነዳጅ ላኪ ሃገር ያደርጋታል፡፡

 
በሁለቱ ሃገራት ያለው የነዳጅ አቅርቦት በሚቀጥሉት ዓመታትም  እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የቻይናው የነዳጅ ኩባንያ ሲኖፔክ በ 2013 ተጨማሪ 10 ሚሊዮን ቶን የነዳጅ ዘይት ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ለመግዛትት ከሩሲያ ጋር መፈራረሙ ይታወሳል፡፡ የቻይናና ሩሲያ ሁለተኛው የነዳጅ ዘይት ቧንቧ መስመር የግንባታ ምዕራፍ በ 2017 መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል፡፡

 

በሌላ በኩል ደግሞ የቻይናና የሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ ቧንቧ መስመር ዝርጋታው ከ ሩብ በላይ የሚሆነው የተጠናቀቀ ሲሆን ይህ ደግሞ ቻይና የተፈጥሮ ጋዝን በደቡብ በኩል ከምትገኘው ጎረቤቷ በኩል በሁለት ዓመታት ውስጥ በቀጥታ መጠቀም ያስችላታል፡፡

ሃገራቱ አዲስ የንግድ አውሮፕላኖች ላይ ትኩረት ሰጥተው ለመስራት በግንቦት ወር ላይ ተስማምተዋል፡፡ አዲሱ አውሮፕላን እንደ ቦይንግ እና ኤርባስ ካሉ ተፎካካሪዎቻቸው ጋር ለመወዳደርም ትልቅ እና ረዥም ርቀት መጓዝ የሚችል እንደሚሆን ነው የተገለፀው፡፡

የፋይናንስ ትብብርን በተመለከተ ቻይና እና ሩሲያ በጋራ የሚያተኩሩበት አዲስ መስክ እንዲሆን  የቻይናው ልማት ባንክ ከሁለቱ ሀገራት ጋር በተያያዙ ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡

ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የቻይና የውጭ ንግድ መጠን 11ነጥብ7 ቢሊዮን ዩአን ወይም 1ነጥብ 77 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሆን ችሏል፡፡

ከቻይና አጠቃላይ የጉምሩክ መረጃ እንደሚያመላክተው በቻይና እና በሩሲያ መካከል የተካሄደው የንግድ ልውውጥ በዚህ ዓመት ውስጥ በመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ብቻ 223 ቢሊዮን ዩአን ደርሷል፡፡ ለዚህም ነው የንግድ ትስስራቸውን ለማጎልበት እየሰሩ የሚገኙት፡፡ ሲል በዘገባው ያስነበበው ሲጂቲኤን ነው ፡፡