ባለሥልጣኑ ከ 750 ሚሊዮን በላይ በሆነ ወጪ የሁለት የመንገድ ግንባታ ውል ፈረመ

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከ750 ሚሊየን በላይ በሆነ ወጪ ከሁለት የሀገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች ጋር ግንባታ ውል መፈራረሙን አስታወቀ ።

የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ  ጥዑመ  ወልደ ገብርኤል የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ግንባታ በሁለት ተከፋፍሎ የሚከናወን ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል ከቦሌ ቡልቡላ እስከ ወረዳ 12 ሁለተኛው  ከወረዳ12 መስቀለኛ መንገድ እስከ ኖቫ ሪል ስቴት የሚዘልቅ  የ3ነጥብ8 ኪሎሜትር እርዝመት  ያለው ነው ተብሏል ።  

የወሰን ማስከበር ስራውን ጨምሮ 24 ወራት የግዜ ገደብ የተቆረጠለት ይህ ፕሮጀክት የኮንትራት ውሉን ያሸነፈዉ ፉል ጀነራል ኮንትራክተር የተባለ የአገር ውስጥ የስራ ተቋራጭ ነው፡፡ 

የፕሮጀክቱን ወሰን ማስከበር ጨምሮ የሁለት ዓመት የግንባታ ጊዜ የተሰጣቸው ሲሆን ፕሮጀክቱን የሚቆጣጠርና አማካሪ ድርጅት መረጣ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡