ኢራቅ ከኦፔክ ጋር ያላት ግንኙነት በመቋረጡ የነዳጅ ጭማሪ ማሳየቱ ተመለከተ

ኢራቅ ከኦፔክ ወይም (አለም አቀፍ ሀገራት የነዳጅ አቅራቢ ሀገራት ድርጅት) ጋር የነበራት  ውል በማቋረጡ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተመለከተ ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ ምርት እና አቅርቦት ቀዳሚ ከሚባሉ ሀገራት መካከል አንዷ እና ዋነኛዋ ኢራቅ ስትሆን ይህቺ ሃገር የነዳጅ ዋጋን ከፍ እና ዝቅ ባደረገች ቁጥር የአለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋም በዛዉ ልክ ከፍ እና ዝቅ ይላል፡፡

አሁንም ኢራቅ ከኦፔክ ጋር የነበራት ዉል በመቋረጡ የነዳጅ ዋጋዉ ሊጨምር መቻሉ  ነዉ የተለያዩ   የመረጃ  ምንጮች  እየዘገቡ  ይገኛሉ ።

የኢራቅ  የነዳጅ ሚኒስትር ቢሮ በሠጠዉ መግለጫ ኦፔክ  እና ሌሎች አለም አቀፍ የሃይድራይት አምራች ኩባንያዎች የአለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋን ለመጨመር እያሰቡ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

በመሆኑም በአለም የተለያዩ አካባቢዎች የነዳጅ ዋጋዉ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የዋጋ ጭማሪው በከፍተኛ ሁኔታ እንደምጨምር በተገመተባት አሜሪካ ግን እንደተፈራው ሳይሆን ዝቅተኛ የዋጋ ጭማሪ ብቻ ማሳየቱም ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ሰአትም የነዳጅ ዋጋዉ በአሜሪካ በበርሜል 34 ሳንቲም የአሜሪካን ዶላር  ብቻ የጨመረ ሲሆን ይህም የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ ወደ 50 ዶላር ከፍ እንዲል አስችሏል፡፡

የነዳጅ ዋጋዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ ቢመጣም አቅርቦቱም በዛዉ ልክ እየጨመረ እንደነበርም መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

የነዳጅ ምርት አቅርቦቱ በፈረንጆቹ መስከረም ወር ብቻ በ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በርሜል ቢያድግም በዚያው ልክ የ470 ሚሊዮን ዶላር የዋጋ  ጭማሪ  አሳይቷል፡፡

አሁን ግን ኢራቅ ዉሏን ማቋረጧን ተከትሎ የፔትሮሊየም ነዳጅ ኤክስፖርት አድራጊ ሀገሮች እና ሌሎች አምራቾች ያቀረቧቸው አማራጮች በአንድ ወር ውስጥ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል፡፡

በዚህ የነዳጅ ዋጋ ንረት ላይ ለመወያየት እና ዉሳኔ ለመስጠት በመጪዉ የፈረንጆቹ መጋቢት ወር ላይ ሃገራቱ በዩናይትድ አረብ ኢሜሬትስ ለመገናኘት ቀጠሮ ተይዟል፡፡

ኦፔክም  ከሩሲያ ነዳጅ  አምራቾች ጋር በመተባበር  የዓለማቀፍ የነዳጅ ክምችቶችን ለማሳደግ የተለያዩ ጥረቶችን ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

በዚህም መሰረት በቀን አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በርሜል  ነዳጅ በማምረት እስከ መጋቢት 2018 ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ንረቱን ጋብ ለማድረግና የሀይል ውስንነትን ለመቀነስ ጥረቶች ይደረጋሉ፡፡(ምንጭ: ሲጂቲኤን)