የቻይና ምጣኔ ሃብት በ2017 6ነጥብ 8 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ተመለከተ

የአለም ባንክ የቻይና ምጣኔ ሀብት በ2017 ከነበረበት ደረጃ የስድስት ነጥብ ሥምንት በመቶ እድገት እንደሚያሳይ አመለከተ ፡፡

ለምጣኔ ሃብቱ ዕድገት እንደምክንያት ያስቀመጣቸው ጉዳዮች ደግሞ የነብስ ወከፍ ገቢ መጨመር እና የውጪ ንግድ መሻሻል ናቸው፡፡

ቻይና የአለማችን ሁለተኛዋ የግዙፍ ምጣኔ ሀብታዊ ባለቤት ነች፡፡ ከጊዜ ወደጊዜም የሀገሪቱ ምጣኔ ሃብት እድገት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

የአለም ባንክ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርትም የቻይና ምጣኔ ሀብት እኤአ በ2017 ከነበረበት ደረጃ የስድስት ነጥብ ሥምንት በመቶ እድገት እንደሚያሳይ ተንብዯል፡፡

ባንኩ ባወጣው ሪፖርት የቻይና ምጣኔ ሀብት እኤአ በ2017 ካስመዘገበው የስድስት ነጥብ ሰባት በመቶ እድገት ወደ ስድስ ነጥብ ስምንት በመቶ ከፍ እንደሚል አመላክቷል፡፡

ይህ የባንኩ ትንበያ ሁለተኛው ሲሆን ባሳለፈነው የአውሮፓውያኑ ግንቦት ወር የቻይናን ምጣኔ ሀብት ከ ስድስት ነጥብ አምስት በመቶ ወደ ስድስት ነጥብ ሰባት በመቶ እድገት እንደሚያሳይ አስቀምጦ ነበር፡፡

ባንኩ ባወጣው ሪፖርት መሠረት ለምጣኔ ሃብቱ እድገት የነብስ ወከፍ ገቢ መጨመር እና የውጪ ንግድ መሻሻል እንደምክንያት አስቀምጧል፡፡

በቻይና የአለም ባንክ ምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ሚስተር ጆን ሊትዋክ የቻይና ባለስልጣናት የማክሮ ኢኮኖሚ ​​አለመመጣጠን ለመቀነስ እና የሀገሪቱን እድገት በማይጎዳ መልኩ የፋናንስ እገዳዎችን በማድረግ  የሀገሪቱን እድገት እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የምጣኔ ሀብት ክፍፍሉ እድገት ያሳየ ሲሆን የነብስ ወከፍ ገቢ እና  ፍጆታም መሻሻል  አሳይተዋል፡፡

ባለሙያው አክውም የሀገሪቱ የውጭ ንግድ እድገት ለምጣኔ ሀብት እድገቱ አዎንታዊ ሚና የተጫወተ ሲሆን የንግድ ስራ አስተማማኝነትም እየተሻሻለ መጥቷል፡፡የስራ እድል ፈጠራም  እድገት እያሳየ ይገኛል፡፡

ባንኩ ባስቀመጠው ግምት መሠረት የሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት አሁን ካለበት ደረጃ በሚቀጥሉት ሁለት ተከታታይ አመታት ወደ 6ነጥብ4 በመቶ እና ወደ 6ነጥብ 3 በመቶ በተከታታይ ቅናሽ  ያሳያል፡፡

ሪፖርቱ እንዳመላከተው ጠንካራ የገንዘብ ፖሊሲ በመከተል ፤  ጥብቅ የፋይናንስ ስርዓት በመዘርጋት እና መንግስት ኢኮኖሚውን መልሶ ለማደራጀትና ቀጣይነት ባለው መልኩ የህብረተሰቡን አቅም ለማጎልበት እያከናወነ ያለው  ጥረት ለምጣኔ ሀብት ዕድገቱ  ጉልህ  አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
ሪፖርቱ እንዳመላከተው የመንግስት በጀት ማሻሻያዎች በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ እና የሀገሪቱ  ጡረታ አሠራር ውጤታማ መሆን  ለማክሮ ኢኮኖሚ ማረጋጋት ፤ለፍትሃዊ የምጣኔ ሀብት ክፍፍል  እንዲሁም  በሚቀጥሉት አመታት ውስጥ ማህበራዊ ለውጦችን ለማስመዝገብ ወሳኝ ናቸው፡፡ (ምንጭ: ሲጂቲኤን )