ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የሜክሲኮ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ መጣላቸውን ይፋ አደረጉ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህገወጥ ስደት ጋር በተያያዘ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የሜክሲኮ ምርቶች ላይ የ5 በመቶ ቀረጥ መጣላቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ቀረጡ ከሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግና በሂደትም ጭማሪ እንደሚደረግበት ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

በሜክሲኮ ምርቶች ላይ የተጣለው ቀረጥ አሜሪካ ከሜክሲኮ በምትዋሰነው ደቡባዊ ክፍል ያለውን ህገ ወጥ ስደት ለመግታት ታሳቢ ያደረገ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ህገ ወጥ ስደቱን ተከትሎ በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋልም ነው የተባለው።

የአሜሪካ ድንበር ጠባቂዎች በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል ያለውን የስደተኞች ፍልሰት መቆጣጠራቸውን ቢገልጹም በስደተኞች አያያዝ ዙሪያ ግን አሁንም ትችትን እያስተናገዱ ነው።

(ምንጭ፡-ቢቢሲ)