በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በደረሰ ጥቃት 29 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በደረሰ ጥቃት 29 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደረሰ።

የከተማዋ የእሳትና ድንገተኛ መስሪያ ቤት በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ባይኖሩም የደረሰባቸው ጉዳት ከፍተኛ ነው ብሏል።

ከንቲባው ቢል ዴ ብላሲዮ ለጥቃቱ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ሆን ተብሎ የተፈጸመ ጥቃት መሆኑን ተናግረዋል።

ከንቲባው የደረሰው ጥቃት የሽብር ጥቃት ስለመሆኑ የሚያመላክት መረጃ እስካሁን አላገኘንም ብለዋል።

የዴሞክራቶቹ እጩ ፕሬዚዳንት ሂላሪ ክሊንተን በደረሰው ጥቃት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ለተጎጅዎች አፋጣኝ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል።

የሪፐብሊካኑ ተፎካካሪ ዶናልድ ትረምፕ በበኩላቸው፥ ከጥቃቱ ጀርባ ማን እንዳለ ባይታወቅም አሜሪካ የከፋ ጊዜ እያሳለፈች ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በኒውዮርክ የደረሰው ጥቃት በኒው ጀርሲ የቦንብ ፍንዳታ ከተከሰተ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ ተነግሯል።(ኤፍ ቢ ሲ)