የደቡብ ኮርያ አቃቢ ህግ በሳምሰንግ ኩባንያ ኃላፊ ላይ 12 ዓመት አሥር ጠየቁ

የደቡብ ኮርያ ዓቃቢ ህግ በሳምሰንግ ኩባንያ  ኃላፊ ሊ ጄ ዮንግ ላይ የ12 ዓመት እስር ጠየቁ ፡፡

ሊ ጄ ዮንግ በሙስና ወንጀል ተከሰው ፍርድቤት መቅረባቸውም የተነገረ ሲሆን፥ግለሰቡ የሳምሰንግ ኩባንያ ሊቀመንበር እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

ሊ ዮንግ በቁጥጥር ስር የዋሉት በየካቲት ወር ሲሆን  እሳቸው ግን ክሱን አስተባብለዋል፡፡ ግለሰቡ የተከሰሱበት ወንጀል ለመንግስት የገንዘብ ድጎማ ሰጥተዋል የሚል ነው ፡፡  የደቡብ ኮርያ ዓቃቤ ህግ እንደተናገሩት ሊ ጄ ዮንግ የሙስናው ቅሌት ዋናው ተዋንያን የነበሩ ሲሆን ከፍተኛ የገንዘብ ተጠቃሚም ነበሩ ብለዋል፡፡

ዓቃቤ ህጉ በወንጀሉ እጃቸው አለበት ብሎ የከሰሳቸው ሰዎች ሊ ዮንግን ጨምሮ አራት የኩባንያው  ሥራ አስፈጻሚዎች ሲሆኑ ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ፓርክ ጉዩን በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው እንዲያሸንፉ በብዙ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አድርገዋል በማለት ክሳቸውን አቅርበዋል፡፡       

ዓቃቢ ህጉ አክለውም ተከሳሾቹ በግል ጥቅማ ጥቅምና ተጠያቂ መሆናቸውንና ከአንዳንድ የመንግስት አካላት ጋር ልዩ ትስስር እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡      

የጉቦው ዋና ዓላማ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ፓርክ ምርጫውን እንዲያሸንፉ ማድረግ እንደነበርም ነው በክስ ጭብጡ ላይ ያብራሩት ዓቃቢ ህጉ ፡፡

በመጨረሻም የሊዮንግ  ጠበቃ  ደንበኛዬ የቀረበበት ክስ ከሃቅ የራቀ ነው ብለዋል፡፡( ምንጭ:ቢቢሲ)