ቻይናና ኢንዶኔዥያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተወያዩ

ቻይና እና ኢንዶኔዥያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግና ለማጠናከር  ውይይት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ ፡፡

ሁለቱ የሩቅ ምስራቅ ሃገራት በቤጂንግ እያከናውኑ የሚገኙት  ውይይት የሃገራቱን የሁለትዮሽ ምጣኔ ሀብታዊ  ስምምነት ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በቻይና እና ኢንዶኔዥያ መካከል ኢኮኖሚዊ ግንኙነቱ የተጀመረው ውይይት እኤአ በ2015 ሲሆን ይህ ሦስተኛው ውይይት በቻይናው የህዝብ ተውካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ያንግ ጂቺ እና በኢንዶኔዥያው የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስተባባሪ ዳርሚን ናሱሺን መካከከል እየተደረገ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም ቻይና የባቡር መንገድ ግንባታን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ተግባራትን  ኢንዶኔዥያ የከናወነች ሲሆን ይህ የአሁኑ ውይይት ዋነኛ አላማ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ነውም ተብሏል፡፡

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ሃገራት ባለስልጣናት የሁለትዮሽ ትብብሩን ለማጠናከር የተስማሙ ሲሆን በተለይም በመሬት አጠቃቀም፣ በግብርና፣ በኃይል አቅርቦት እና በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ ወደ ባንዱንግ የሚደርስ ባቡር መስመር ዝርጋታ ለመስራትና በኢንዶኔዥያ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ቻይና የኢንዶኔዥያ ሶስተኛ የምጣኔ ሃብት ምንጭ በሆነው የቱሪስት ዘርፍ ላይ ከሃገሪቱ ጋር በጋራ የመሥራት ጽኑ ፍላጎት አላትም ተብሏል፡፡  

ሁለቱ ሃገራት በዚህ  የኢኮኖሚ ውይይታቸው ላይ በኢንዶኔዥያ ለሚሰሩ የመሰረተ ልማት ሥራዎች ቻይና የገንዘብ ድጋፍ የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርግም ተስማምተዋል፡፡( ምንጭ:ሲጂቲኤን)