በካታላን ግዛት ህዝበ ውሳኔ አካሄደች

በስፔን  ካታላን  ግዛት  ህዝበ ውሳኔ  ማካሄዷ ተገለጸ ።   

በህዝበ ውሳኔው የካታላን ግዛት ከስፔን ተገንጥላ ነፃ ሀገር እንድትመሰርት የሚያስችል አብላጫ ድምጽ አግኝቷል፡፡

በሰሜን ምስራቅ የካታሎኒያ ግዛት በሃብት ክምችቷ የስፔንን ምጣኔ ሃብት አንድ አምስተኛውን የምትይዝ ስትሆን ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይኖርባታል፡፡

ግዛቷ ነጻ ሃገር ትመስርት ወይስ ከስፔን ጋር ትቀጥል የሚለውን ለመለየት ህዝበ ውሳኔ  አካሂዳለች፡፡

በህዝበ ውሳኔው መሠረትም የካታላን ግዛት ነዋሪዎች ግዛቷ ከማድሪድ ማዕከላዊ መንግስት ተገንጥላ ነጻ ሃገርና መንግስት እንድትመሰርት የሚያስችል ድምጽ ሰጥተዋል።

2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች ድምጽ በሠጡበት ህዝበ ውሳኔ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ ሠጭዎች ግዛቲቷ ራሷን የቻለች ሃገርና ነጻ መንግስት እንድትመሰርት ደግፈው ድምጽ መስጠታቸውን የካታላን ግዛት ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የስፔን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕዝበ-ውሳኔውን ሕገ-ወጥ በማለት ውድቅ አድርጎታል።

የስፔን ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ህዝበ ውሳኔውን ቢያግደውም በሺዎች የሚቆጠሩ የግዛቲቱ ነዋሪዎች ድምፅ ሰጥተዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም ፖሊስ ሕዝበ-ውሳኔውን ለመከልከል ሲሞክር ከድምፅ ሲጪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል፡፡

የካታሎንያ ግዛት መንግስት እንደሚለው ከሆነ ከ800 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በግጭቱ ምክንያት መሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የስፔን የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ ግጭቱን ተከትሎ 12 ፖሊሶች ጉዳት መድረሱን ገልጿል፡፡

የህዝበ ውሳኔውን ተከትሎም በስፔንና በካታላን ባለስልጣናት መካከል አለመግባባትና ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ተነግሯል፡፡

የካታላን መሪ ካርልስ ፑዪግዴሞን የመንግሥትን እርምጃ በተለይም የፖሊስ  እርምጃ ጭካኔ የተሞላበት ነው ሲሉ ኮንነዋል።

ያም ሆን ይህ ግን በጉጉት ስንጠብቀው የነበረውን ራስን በራስ የማስተዳደር እና ሪፐብሊክ የመመስረት ፍላጎታችንን በድምጻችን አስከብረናል ብለዋል።

ምንም እንኳ መሪው በህዝበ ውሳኔው የስፔኗ ካታሎኒያ ግዛት ራሷን ችላ እንደ ሀገር እንድትቋቋም ያድርገናል ቢሉም የስፔን መንግስት ግን ጉዳዩ ህገወጥ በመሆኑ ተቀባይነት አያገኝም ብሏል፡፡

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራጆይ ካታሎናውያን ህገ ወጥ በሆነ የህዝበ ውሳኔ ላይ ድምጽ በመስጠታቸው መሸወዳቸውን ልገልጽ እፈልጋለሁ ብለዋል።

በካታሎኒያ ነፃ ሀገር ብሎ ነገር የለም በዚህ ላይም እውቅና ኖሮት የተካሄደ ህዝበ ውሳኔ የለም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ተከትሎ የግዛቷን መገንጠል የሚደግፉ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ አሰምተዋል።

እናም የካታሎንያ ነጻ አገር የመሆን ውጥን የተሳካ ቢመስልም ውዝግቡና አነጋጋሪቱ ግን እንደቀጠለ ነው አልጀዚራ እንደዘገበው፡፡