የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ጋዛን እየጎበኙ ነው

የፍልስጤም ጠቅላይ ሚንስትር ጋዛን እየጎበኙ መሆኑ ተገለጸ ።

ታሪካዊ የተባለው የፍልስጤሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ራሚ ሃምዳላህ ጉብኝት በዌስት ባንክና በጋዛ አስተዳደር መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ይፈተዋል ተብሎ ተጠብቋል፡፡

በተለይ ሰሞኑን በሃማስና ፋታህ አመራሮች መካከል የመከፋፈል አደጋ  ተፈጥሮ እንደነበር ተነግሯል፡፡    

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጉብኝት ወደ ጋዛ ሰርጥ ያመሩትም በፍልስጤሙ ፕሬዝደንት መሃሙድ አባስ ትእዛዝ መሰረት መሆኑ ታውቋል፡፡

እናም የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ይህን የመከፋፈል ስጋት ወደ አንድ ለማምጣት አንዱ ጥረት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ራሚ ሃምዳላህ ከጋዛ ሰርጥ ጉብኝታቸው ባስተላለፉት መልዕክት የፍልስጤም ህዝብ አንድ ሆኖ ልማቱንና ሰላሙን ማረጋገጥ አለበት ብለዋል።

ዌስት ባንክ ያለጋዛ ጋዛ ሰርጥም ያለ ዌስትባንክ እንደሃገር ለመቀጠል በፖለቲካውም በጂኦግራፊውም አስቸጋሪ በመሆኑ ልዩነቶችን አጥብበን ውህደት በመፍጠር ታላቋን ፍልስጤም መመስረት አለብን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ፍልስጤም እንደሃገር ለመቀጠልና የዌስት ባንክን የፖለቲካ ስርዓት አስጠብቆ ለመጓዝ ያለው ብቸኛ አማራጭ አንድነት መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጋዛ ሰርጥና ከዌስት ባንክ የተውጣጣ የጥምር መንግስት በቅርቡ በጋዛ ሰርጥ ስራውን እንደሚጀምር ገልጸዋል።(ምንጭ:  የሮይተርስ )