የብሪታኒያው መከላከያ ሚንስትር ማይክል ፎንን በጾታዊ ትንኮሳ ክስ ምክንያት ከኃላፊነት ተነሱ

የብሪታኒያው የመከላከያ ሚኒስትር ማይክል ፎለን በሴቶች ላይ የፆታዊ ትንኮሳ ፈጽመዋል በሚል የሀገሪቷ ፓርላማ ባነሳባቸው ጥያቄ ምክንያት ራሳቸውን ከመንግሰት ኃላፊነት  አንስተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ከተቀበልኩት የመንግስት ኃላፊነት አንፃር የፆታዊ ትንኮሳው  ሀሜት እና ክስ የሚገባ አይደለም፡፡ ይህን ተግባር ከፈፀምኩኝ ደግሞ የመከላከያ ሚኒስቴርን መምራት አይገባኝም በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል::

ሰውየው የትምህርት፣ የንግድ እና ኢንተርፕራይዝ እንዲሁም የኢነርጅ ሚኒስትር ሆነው ብሪታኒያን ያገለገሉ ናቸው፡፡ ከፈረንጆቹ 2014ዓ.ም ጀመረው ደግሞ የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሀገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

ማይክል ፎለን በመካከለኛው ኢስያ የተንሰራፈውን ሽብርተኝነት ለማዳከም ትልቅ ስራን እንደሰሩም በርካቶች ይመሰክሩላቸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ካቢኔ መሪ ተዋናይ እና ቀኝ እጅ የሆኑት የመከላከያ ሚኒስትሩ ማይክል ፎለን ብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት እንድትገነጠልም ትልቅ ስራ የሰሩ ናቸው ይባላል፡፡

ማይክል ፎለን ይህን ሁሉ ተግባር ለሀገራቸው ቢያከናውኑም አዕምሯቸው በጎለመሰ ሰዎች ፊት ልፋታቸውን ሁሉ ገደል የሚከት አንድ አመል እንዳለባቸው ግን በርካቶች ይስማማሉ፡፡ይህም ሴቶች ያለፍቃዳቸው መትንኮሳ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ካለጉንተላ የማይሆንላቸው የሚመስሉት ሚኒስትሩ በዚህ ድርጊታቸው የብሪታኒያ ፓርላማ ተደጋጋሚ ወቀሳ አቅረቦባቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋቸዋል ይባላል፡፡

ከሀገሪቱ እንደራሲዎች ምክር ቤት ግፊት የበረታባቸው መከላከያ ሚኒሰትሩ  ህገወጥ ተግባራቸውን በማመን የብሪታኒያ የመከላከያ ሚኒስትርነት የሚሻውን ስዕብእና ስላላሟላው ሀገሬን አዋርጃለሁ በማለት የመልቀቂያ ደብዳቢያቸውን ለሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ጽህፈት ቤት አስገብተዋል፡፡

ማይክል ፎለን የጾታ ትንኮሳ ክሱ የተመሰረተባቸው በተለይ በብሪታኒያ ፓርላማ ሴት አባላት እና ታዋቂ የፊልም ሴት ተዋናዮች ላይ በተደጋጋሚ በሚያደርሱት ፆታዊ ትንኮሳ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ሚኒስትሩ በመለቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ እንደፃፉት ከሆነ አሁን እየፈፀምኩት ያለው ርካሽ ተግባርና የተመሰረተብኝ ክስ የብሪታኒያ የመከላከያ ኃይልን ደረጃ የማይመጥን ተግባር በመሆኑ በገዛ ፍቃዴ ስልጣኔን ለመልቀቅ ወስኛለሁ ብለዋል፡፡

ማይክል ፎለን ከዚህ ቀደም ከሴቶች ፆታዊ ትንኮሳ ጋር የተያያዘ ተደጋጋሚ ክስ ቀርቦባቸው የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2002 እንኳን ከአንድ የሬድዩ ጋዜጠኛ ጋር ቃለ ምልልስ እያደረጉ የጋዜጠኛዋን ጭን ባልታሰበ መልኩ በመንካት የፆታዊ ትንኮሳ እንደፈፀሙ በፓርላማው ተነስቷል፡፡

ፎለን ይህንን ተግባርም በማመን ስልጣናቸውን ሲለቁ በጋዜጠኛዋ ላይ ለፈፀሙት አስነዋሪ ተግባር ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

ሚኒስተሩ የሆሊውድ የፊልም ፕሮዲውሰር በሆነችው ሀርቪ ዊስተን ላይ ፆታዊ ጥቃት አድርሰዋል በመባልም ክስ ቀርቦባቸው ነበር፡፡

በዚህ መጥፎ ልማዳቸው የተነሳ ማይክል ፎለን በብሪታኒያ የፖለቲካ ታሪክ ውሰጥ በፆታዊ ትንኮሳ ምክንያት ስልጣናቸውን በይፋ ያጡ ብቸኛው ሚኒስተር ለመሆን በቅተዋል፡፡

የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ፎለንን በፈጸሙት ጸያፍ ተግባር ክስ ሊመሰርትባቸው የተለያ ማስረጃዎችን ያሰባሰበ ሲሆን ፎለን ግን የምጠየቅባቸው ጥፋቶችን አውቃቸዋለሁ፡፡ በአብዛኞቹ ሀሰት እና መሰረተ ቢስ ናቸው በማለት ክሱን እንደማይቀበሉት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስት ቴሬሳ ሜይ የማይክል ፎለንን የመልቀቂያ ደብዳቤ ከተቀበሉ በኋላ ሰውየው በስልጣን ዘመናቸው በሶሪያ እና በኢራቅ ተንሰራፍቶ ለነበረው አይ ኤስ አይ ኤስ ለተባለው አሸባሪ ቡድን መዳከም ላበረከቱት አስተዋጽኦ  ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከዚህ ክስተት  በኋላ በብሪታኒያ እየተስፋፋ የመጣውን የሴቶች ፆታዊ ትንኮሳ እና ጥቃት ለማስቆም ካቢኒያቸውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡

የማይክል ፎለንን ቦታ የሚተካ ሰው እስከ ከነገ በስተያ ድረስ ይፋ ይሆናል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡