ሳውዲ አረቢያ ዜጎቿ በፍጥነት ሊባኖስን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላለፈች

ሳውዲ አራቢያ ዜጎቿ በፍጥነት ሊባኖንን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ አስተላለፈች፡፡

ሀገሪቷ ይህን ጥሪ ያስተላለፈችው በቅርብ በሰኡዲ አራቢያ የአየር ክልል ውስጥ በተገኘው ሚሳኤል እና በቀጠናው ላይ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል ያለው የሺቲ ሚሊሺያ መጠናከርን ተከትሎ ነው፡፡

አሁን በሳውዲ አራቢያና ሌሎች የቀጠናው ሀገራት መካከል ጦርነት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ያለው ውጥረት አሁን አሁን እያየለ መጥቷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ሳውድ አራቢያ በአየር ክልሏ ሲምዘገዘግ ያየችው ሚሳኤል ያስከተለው ቁርሾ በቀጠናው ላይ እልቂት ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል፡፡ ለዚህ ደግሞ በርካታ መላ ምቶች እየተነሱ ይገኛሉ፡፡

 ሳውዲ አራቢያ አሁን በተለይም በሊባኖስ የሚገኙ ዜጎቿ በፍጥነት ሀገሪቷን ለቅቆ እንዲወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋለች፡፡ ሀገሪቷ ይህነ ልታደርግ የፈለገችው አሁን በቀጠናው ላይ እየታየ ባለው ውጥረት በአካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ቀውስ ዜጎቿን እንዳያጠቃ ነው፡፡

አሁን የሰውዲው ንጉስ ለዜጎቻቸው ይህን መልዕክት ሲያስተላልፉ ከሙስና ጋር በተያያዘ ከ200 በላይ የሚሆኑ የሳውዲ ዜጎችን  ዘብጥያ ሲጥሉ 11 የሚሆኑትን የንጉሳዊያን ቤተሰቦች ላይ ደግሞ ምርመራ እያከሄዱ ይገኛሉ፡፡

ንጉሱ ይህን እርምጃ የወሰዱት ከየመን ወደ ሪያድ የተተኮሰው ሚሳኤል ጉዳይ ሳይረግብ በሰዓታት ውስጥ ነው፡፡

ንጉስ ሞሃመድ ቢን ሳላህ ደግሞ በሊባኖስ የሚገኙ ሳውዲዎችን በቶሎ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ አስጠንቅዋል፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በሳውዲ እና በሁለቱ የአረብ ሀገራት ሊባኖስ እና በኢራን መካከል ውጥረት በመፈጠሩ ነው፡፡ በእርግጥ በኢራን እና በሰውዲ መካከል ከሁለት አስርት አመታት በላይ ያስቆጠር ኩርፊያ ያላቸው ቢሆንም የሳምንቱን የሚሳኤል ሙከራን ሚሊሻው ሪያዲን እንዲያጠቃ ኢራን አመቻችታለች የሚል አሜኔታ የሳውዲው ንጉስ እንዳላቸው የወጣው ዘገባ አትቷል፡፡

የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲል ጃቢር ጉዳዩን በተመለከተ ለሲ ኤን ኤን እንደተናገሩት ሳውዲ ጉዳዩን ወታደራዊ እርምጃ እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡

ኢራን ይህን ማድረጓ ሞኝነቷ ነውም ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሂዝቦላና ኢራን በሳውዲ ላይ ጥቃቱን ለማድረስ ሲሞክሩ ሊባኖስ ሂዝቦላን መቆጣጠር እየቻለች ችላ ማለቷ ደግሞ ሰውዲ በሊባኖስ ላይ እንድታቄም አድርጓታል፡፡

ንጉስ ሞሃመድ ቢነ ሳለማን በመካከለኛው  ምስራቅ ምድር ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ እና አሁን በሚሳኤል ለሞከራችው  አገር ወታደራዊ ምላሽ ለመስጠት አስበው እየተዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ የፖለትካ ባለሙያዎች እና መንግስታት አጥጋቢ አይደለም ሲሉ እየሞገቱ ነው፡፡

ሳውዲ ከሊባኖስ ጋር በየጊዜው እሰጣ ገባ ውስጥ በምትገባ ወቅት ለበርካታ ጊዜ የሰውዲ ተወላጆች ሊባኖስን ለቅቀው እንዲወጡ ስትወተውት በአራት ኣመት ጊዜ ውስጥ ይህኛው ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑን ያስታዋሰው ዘገባው በእነዚህ ጊዜ ውስጥም ወታደራዊ እርምጃ ወስዳ አታውቅም፡፡

ከዘህ በፊት ሳውዲ አራቢያ ከእስራኤል ጋር በመሆን በቀጠናው የኢራንን የበላይነት ለማርግብ በነበረው እርምጃ ላይ ትልቅ ሚና ተጫውታለች፡፡ ይህ ደግሞ በሌላ በኩል ሂዝቦላ ኢራን እና ሊባኖስ አንድ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ እውቅና የሌለው የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን እንዲጠናከር ረዳው፡፡ ይህ ደግሞ አሁን ሳውዲ ለመውሰድ እየተዘጋጀች የምትገኘውን እርምጃ በወቅቱም ለመውሰድ ስትዳዳ ነበር፡፡

እስራኤል በበኩሏ በቀጠናው ላይ ኢራን፣ ሊባኖስ እና ሂዝቦላ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው ብላ ታምናለች፡፡ ሰውዲም ከዚህ ተለየ ሓሳብ የላትም፡፡ በመካከለኛው ሀገር ውስጥ ሀያል የሆኑት ሁለቱ ሀገራት የቀጠናው አስቸጋሪ ተብለው የተፈረጁት ሂዝቦላና ሊባኖስ እና ኢራን ራሳቸውን ለጦርነት ያዘጋጁ ናቸውም አሁን እንደሚያምኑ ታውቋል፡፡

ንጉስ ሞሃመድ ቢን ሳላህ በመካከለኛው ምስራቅ በሚወስዱት ማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ እና የበላይነታቸውን ለማስጠብቅ በተለይም ዋና አጋሮቻቸው ሆኑትን አሜሪካና እስራኤል ይተማመኑባቸዋል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በሪያድ ላይ በተቃጣው የሚሳኤል ጥቃት ሙከራ እስራኤል በጥንቃቄ መታየት ያለበት ብትልም አሁን ንጉሱ ለመውሰድ እየተዘጋጁ ላለው እርምጃ ግን እስካሁን በአሜሪካ በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡

ሆኖም ትራምፕ በኢሲያው ምድር ጉበኝት ላይ ናቸው፡፡ በተገኘው አጋጣሚ ግን በቲዊተር ገፃቸው ለሰውዲ የሚደረገው ድጋፍ የተወሰነ እንዳልሆነ የሚጠቅሙ ዘገባዎች ሲወጡ በሊባኖስ የአሜሪካ አምባሳደር ሆኑት ሪቻርድ ሊባኖሱን የጦር ጄኔራል አግኝተው መነጋገራቸውን የሚያሳይ ፎቶግራፍን በራሳቸው ገፅ ላይ ለጥፈዋል፡፡

አሁን የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳድ ሃሪሪ ጉዳዩን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት እየጣሩ ቢሆንም ጥያቄ ውስጥ የገባው ግን ንግሱ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ዜጎቻቸው ከሊባኖስ እንዲወጡ ሲያደርጉ ባለሁለት ዜግነት ባለቤት የሆኑት መልስ አላገኙም፡፡