ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እስራኤል ከፓላስታይን ጋር ያላትን ግንኙነት ሰላማዊ ማድረግ እንዳለባት ተናገሩ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኒታንያሁ በፈረንሳይ መገኘታቸውን ተከትሎ ከፓልስታይን ጋር ያላቸው ጉዳይ በሰላም መጠናቀቅ እንዳለበት ገለጹ፡፡      

ኔታንያሁ በበኩላቸው የትራምፕ ውሳኔ እውን እንዲሆን ጥረታቸውን ቀጥለዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ ዛሬ ከሚደረገው የአውሮፓ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ አስቀድመው ፓሪስ ተገኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቅርቡ ያስተላለፉትን እየሩሳሌምን ወደ እስራኤል የማጠቃለል ውሳኔ ለህብረቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን ያግባባሉ ነው የተባለው፡፡

ማክሮን እንደገለጹት በእስራኤል ላይ የሚደረገውን ማንኛውንም የሽብር ጥቃት እንደሚቃወሙ ገልፀው ነገር ግን የትራምፕ ውሳኔ ለሰላም ድርደር እንቅፋት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ማክሮን እስራኤል በእየሩሳሌም የምታደረገውን የሰፈራ ግንባታ አስቀድማ ማቆም እንዳለባት ገልፀው ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንየሁ ፓላስታንያውን ላቀረቡት ቅሬታ አወንታዊ የሆነ ምላሽ እንዲኖራቸው ጠይቀዋል ነው የተባለው፡፡ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ በሰላም ድርደር ብቻ መፈታት ያለበት ስለመሆኑ ክሮን በአፅኖት ገልፀዋል፡፡

በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ባሳለፍነው ሳምንት ትራምፕ ያስተላለፉትን ውሳኔ ተቃውመዉታል፡፡እስራኤል እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ለማድረግ የምትፈልግ ሲሆን ፓልስታይንም ምስራቃዊ የከተማዋን ክፍል የወደፊት ዋና ከተማቸዉ ለማድረግ ትፈልጋለች፡፡

የትራምፕን ውሳኔ ተከትሎ የተለያዩ ያለም ሀገራትም በተመሳሳይ የእየሩሳሌም ጉዳይ ለድርድር ክፍት መሆን እንዳለበት ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ናቸው ፡፡ ሆኖም የትራምፕ አስተዳደር በቀጣይ የሚደረጉ ድርድሮች እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ ባደረገ መሠረት መሆን እንዳለበት አስቀምጧል፡፡ እናም ቀደም ሲል የወጡ ፖሊሲዎች መተግበር ለሰላም ድርድሩ መሠረት እንደሆነም ያስቀምጣል፡፡

ኒታያንያሁ ፓልስታይን እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ የመሆኗን እውነታ ካልተቀበለች የሰላም ድርደር ሂደቱን እንደሚያኮላሸው ለማክሮን በምላሻቸውን ገልጸዋል፡፡ለሚፈለገው ሰላም አንደኛው  ወገን አስቀድሞ ከድርድሩ ሊወጣ እንደሚችል ቅደመ ማስጠንቀቅያ ከወዲሁ የሰጡ ሲሆን እየቀረበ ያለውን ተቃውሞም የሰላም ድርደሩን የሚሸረሽር ነው ብለዉታል፡፡

ኒታንያሁ መሐሙድ አባስ  ወደ ሰላም ድርደር ጠረፔዛ እንዲመጡ ጥሪ አቅረበው ሆኖም ግን ድርድሩ ቀላል ሊሆን እንደማይችል ከወዲሁ አንስተዋል፡፡

ማክሮን በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ፈረንሳይ ካደረገችው የሰላም ማደራደር ሚና ባሻገር ሌላ ተጨማሪ የተለየ ጥረት ማድረግ እንደማይጠበቅባት እንስተዋል፡፡ትራምፕ ያስተላለፉትን ውሳኔ ተከትሎ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲብ ታይብ ኤርዶሃን ያሰሙትን ወቀሳ ኒታንየሁ አጣጥለውታል፡፡ 

አያይዘውም ኒታንያሁ ከአረብ ሀገራት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት አክራሪዎችን ለማስወገድና ኢራንንም ለመገዳደር እንደሚረዳቸው አክለው አንስተዋል፡፡ ኢራን በአሁኑ ሳዓት በሶርያ ውስጥ ረሷን በዘመናዊ መሣርያ አጠናክራ እስራኤልን ለማጥፋት ያላትን ፍላጎት በዝምታ የሚመለከቱት አለመሆኑንና እርምጃ እስከመውሰድም ሊገፉበት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
(ምንጭ:ሲጂቲኤን)