ፑቲን በሶሪያ የተሠማራው ወታደራዊ ኃይል እንዲወጣ ትዕዛዝ ሠጡ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሶሪያ የተሰማራው የሩስያ ወታደራዊ ኃይል  እንዲወጣ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ውሳኔዉን ያስተላለፉት የአገራቸው ወታደራዊ ኃይል በደማስቆ የተለያዩ የሽብር ጥቃቶችን ሲፈፅም የነበረውን አሸባሪ ድርጅትን ለመደምሰስ የተሠጠውን ተልዕኮ በማጠናቀቁ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ፑቲን በሶሪያ ላታኪያ ግዛት የሚገኘውን የሂመይሚን የአየር ሃይል ጣቢያ ሳይጠበቅ ከጎበኙ በኋላ ከሶሪያው አቻቸው ጋር በመነጋገር ትዕዛዙን መሥጠታቸው ነው የተሰማው፡፡

ሩሲያ እኤአ በ2015 የፕሬዚዳንት በሽር አላሳድን መንግስት በመደገፍ በሶሪያ ወታደራዊ ኃይል በማሰማራት የበኩሏን አስተዋፅኦና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በተግባር ማሳየቷን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡