የፍልስጤም ነጻ አውጪ ድርጅት እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና እንደማይሠጥ አስታወቀ

የፍሊስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ስለመሆኗ እውቅና  እንደማይሠጥ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ እውቅናውን አለስጥም ያለው አስራኤል ለጋዛ ሠርጥ እና ዌስት ባንክ እውቅና መሥጠት አለባት በሚል አቋም እንደሆነ ነው ያስታወቀው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ድርጅቱ የአካባቢውን ደህንነት ለማስጠበቅ ከእስራኤል ጋር በጋራ ለመስራት ተብሎ የተቀመጠው ውሳኔ መፍረስ እንዳለበት እና የፍልስጤሙ ምድር በአረብ ሊግ ሥር መካተት አለበት ሲልም አቋሙን ይፋ እድርጓል፡፡ 

እስራኤል እና ፊልስጤም በጋዛ ሰርጥ ምድር የላይ ያላቸዉን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት ያደረጉት እ.ኤ.አ በ1993 ነበር፡፡

ሁለቱ ሀገራት ይህን ስምምነት ያደረጉት በኖርዌይ ከተማ ሲሆን በስምምነቱ መሠረት ዌስት ባንክ የፍልስጤም ከተማ እንድትሆን ሲሆን ከፊል የምስራቁን የእየሩሳሌም ክፍል የያዘው ጋዛ ሰርጥ ደግሞ ከአስራኤል ወታደር ነፃ ሆና በአካባቢው ላይ ያለዉን ውጥረት ለማርገብ አዲስ በፊሊስጤም ለሚቋቋመው አስተዳደር ስልጣኑን በመስጠት በጊዜያዊነት እንዲተዳደር የሚል ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ለጊዜው  አልተከበረም፡፡

የፍልስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት በፍልስጤም ሁለተኛው ህግ አውጪ አካል ጉዳዩን ሲመረምር ከቆየ በኋላ የእየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማ ስለመሆኗ እውቅና ለመስጠት መቆጠቡን አስታውቋል፡፡

እንደ ድርጅቱ አቋም ውሳኔው የአሜሪካዉን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የእየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ስለመሆኗ እውቅና መስጠት እና ኢምባሲያቸዉን ከቴልአቪቭ ወደ እየሩሳሌም ለማስተላለፍ መወሰናቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ፍልስጤም እና እስራኤል በኦስሎ የተፈራረሙት ውሳኔ ጊዜው አልፎበት በጊዜው ያልተከበረ እና ያልተተገበረ ቢሆንም አሁን መታየት እንዳለበት ነው ያስታወቀው፡፡

ሁለቱ ሀገራት ጉዳያቸዉን በሰላማዊም ሆነ በጦርነት ችግራቸዉን መፍታት ከተሳናቸው ከ70 ዓመት በላይ እንደሆነ ይነገርላቸዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት ያልተግባቡበት ጉዳይ ላይ የአሜሪካ አዋጅ በሁሉም የፍሊስጤም ዜጎች ዘንድ አንድ አይነት ድባብ እንደፈጠረም ነው ድርጅቱ አሁን ይፋ ያደረገው፡፡

የፍስጤም ነጻ አውጪ አሜሪካን የእየሩሳሌምን በተመለከተ ይፋ ያደረገችውን እውቅና ሊከላከል በሚችልበት ስትራቴጂ ላይ ህጎችና ደንቦችን ሲያወጣ ሲያወርድ እንደቆየ ተነግሯል፡፡

 ዋፋ የተባለ የፊሊስጤም ዜና ኤጄንሲ እንዳስነበበው አሜሪካ የሁለቱን ሀገረት የረጅም ጊዜ ግጭት እልባት ለመስጠት ብላ የወሰነችዉን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ አለመቀበሉን አስንበቧል፡፡ ድርጅቱ አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሌላ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ፍትሃዊ ውሳኔ እፈልጋለው ማለቱንም ጠቅሷል፡፡

የፕሬዝዳንት ሞሃመድ አባስ  በንግግራቸው ፍልስጤም እና እስራኤል ግዛቶቹን በተለመከተ እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር በ1993 እና 1995 ገለልተኛ የሆነ አካል በፍልስጤም በማቋቋም ይዳኝ  ቢሉም አልተከበረም፡፡

 ከዚህም በተጨማሪ የኦስሎው ስምምነት እስራኤል በፍልሲጤም ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ የበላይነት ለፍሊስጤማውያን ህዝብ እንድትተተው የሚል ነው፡፡

የቀጠናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ደግሞ ከሁለቱ አካላት የተውጣጡ ሰላም አስከባሪ ቡድን እንዲቋቋም የሚለው ደግሞ ሌላው የኦስሎ ስምምነት ነው፡፡ ይሁን እንጅ ችግሩም አልተፈታም ስምምነቱም አልተከበረም፡፡

የፊሊስጤሙ መንግስት ሁለቱ ሀገራት ለ70 አመታት ሲፋጁበት ለነበረው ችግር መፍትሄ ሊሆን የሚችለው ብቸኛው መንገድ ምስራቁን እየሩሳሌም ክፍል ለፍልስጤም፣ ዋና ከተማ አድርጎ እውቅና መሥጠት ነው ሲልም ያምናል፡፡

አሁን የፊሊስጤም ነፃ አውጪ ድርጅት ለትራምፕ እውቅ አይሠጥም ፤አይሆንም የሚል የማያወላውል መልስ መስጠቱን ያስታወቀ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የቀጠናውን ሰላም ለማስከብር የተቋቋመው የጋራ ግብረ ኋይል ከእስራኤል በመላቀቅ ወደ አረብ ሊግ መግባት አለባት ሲልም ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰምቷል፡፡

ድርጅቱ ይህን የመሰለ አቋሙን ሲያስታውቅ እስራኤል በበኩሏ እስካሁን ያለችው ነገር የለም፡፡ በርግጥ ሁለቱ ሀገራት በኦስሎ ስምምነት ሲያደርጉ ይዞታው ለፍሊሲጤም እንደሚገባ የሚያሳይ አዝማሚያ ቢኖርም በተለይም እስራኤል ይዞታዋን ከማጠናከር በላይ ያደረገችው ነገር እንዳልነበረ ዘገባው ያመለክታል፡፡

 ሁለቱ ሀገራት የይገባኛል ጥያቄያቸውን በማቅረብ ላይ እያሉ እንኳ ጥያቄ ውስጥ ባለችው እየሩሳሌም ውስጥ ከ6 መቶ ሺህ እስከ 750 ሺህ የሚደርሱ እስራኤላዊያን እንደሚኖሩ የዘገበው አልጄዚራ ነው፡፡