በንደን ከተማ በግሬንፌል የመኖሪያ ህንጻ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሰዎች ሲሞቱ 70 በላይ ቆሰሉ

በእንግሊዝ ለንደን ከተማ የሚገኝ ግሬንፌል የመኖሪያ ህንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ እስካሁን የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የለንደን ከተማ ፖሊስ ኮማንደር ስቱዋርት ኩንድይ፤በምእራብ ለንደን የሚገኘው ባለ 24 ወለል ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ላይ “እስካሁን 6 ሰዎች መሞታቸውን ላረጋግጥላቹ እችላለው፤ ሆኖም ግን የነብስ አድን ስራ በሚጠናቀቅበት ወቅት የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል” ብለዋል።

በስፍራው የደረሱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በርካታ ቁጥር ያለው ሰው ማትረፍ የቻሉ ሲሆን፤ እስካሁን ከ50 በላይ  ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የተመለከተው ፡፡

 “የተጎጂዎችን ማንነት መለየት ጊዜ ሊወስድ ይችላል” ያሉት ኮማንደሩ፤ “የእሳቱ መንስኤ እንዲህ ነው ብሎ ለመናገርም ጊዜው ገና ነው” ብለዋል።

ከእሳት አደጋው ተርፈው መውጣት የቻሉ ከ70 በላይ ሰዎች ወደ ህክምና ስፍራ ተወስደው ህክምና የተከታተሉ ሲሆን፤20 ሰዎች ደግሞ አስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንደገለጹት፤ ህንጻው ከስር እየጋየ በነበረበት ሰዓት ህንጻው ላይ የነበሩ ሰዎች ለእርዳታ ጥሪ ድምጽ ሲያሰሙ እና ልጆቻቸውን እንዲያድንሉቻው በመማጸን በመጮህ ላይ ነበሩ።

እሳቱ እኩለ ሌሊት ላይ እንደተነሳ የጠቆሙት የዓይን እማኞች፤ በመጀመሪያ የሞባይል ስልክ አሊያም የባትሪ ብርሃን የሚመስል ብርሃን አየን ይላሉ።

በኋላ ላይም ህንጻው ላይ የሚኖሩ ሰዎች በመስኮታቸው በኩል በመውጣት ድረሱልን አድኑን እያሉ መጨው ጀመሩ፤ የተወሰኑት ነዋሪዎች ደግሞ ልጆቻቸውን አዝለው ነበር ብለዋል።

በርካታ ሰዎችም በእሳቱ ታግተው ህንጻው ውስጥ መቅረታቸውንም ገልጸዋል።

እስካሁን እሳቱ ያልጠፋለት ባለ 24 ወለል ህንጻው ሊደረመስ ይችላል የሚል ስጋት የፈጠረ ሲሆን፤

የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ በደረሰው አደጋ እና በጠፋው የሰው ህይወት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

(ቢቢሲ)