ስፔን ከአስርት ዓመታት በኋላ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ እያስተናገደች ነው

የዓለማችን ከፍተኛ የወይራ ዘይት አምራች የሆነችው ስፔን ከአስርት ዓመታት በኋላ ከፍተኛ የሆነ ድርቅ እያስተናገደች ነው፡፡

አሁን  የተከሰተው ድርቅ በወይራ ዘይት ምርትና በሀገሪቱ አርሶ አደሮች ህይወት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን  አልጀዚራ በዘገባው አሳይቷል፡፡

ድርቅ በአብዛኛው በአፍሪካ ባሉ ሀገራት በተለይ ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን በማጥቃቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ዜጎች የእርዳታ እጅ ጠባቂ እንዲሆኑ ያስቻለ ክስተት ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ የተፈጥሮ ክስተት ምጣኔ ሀብታቸው የተሻለ ደረጃ ላይ በሚገኝ ሀገራትም ቢሆን ችግሩ አሳሳቢ  ስለመሆኑ በስፔን የታየው የድርቅ ሁኔታ አመላካች ነው፡፡

ዘመናዊ የእርሻ ስራን በምታከናውነው ስፔን በታሪኳ ሁለት የተፈጥሮ አደጋዎችን አስተናግዳለች፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የደረሰው  ድርቅ ግን ከአሁን ቀደም ከደረሰው አስከፊው እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

በዚህም ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ አርሶ አደሮች ችግር ላይ እየወደቁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስፔን የዓለማችን ከፍተኛ የወይራ ዘይት አምራች ሀገር ነች ፤ይሁንና አሁን ድርቅ ባስከተለው ጉዳት ምርቱ እያሽቆለቆለ ስለመሆኑ ነው በዘርፉ ያሉ አካላት የሚናገሩት፡፡

አርሶ አደር ሚጌል ቪዳ የወይራ ዘይትን ለማምረት የሚረዱ የእፅዋት ዛፎችን ያመርታሉ ይሁንና አሁን በሀገሪቱ የደረሰው ድርቅ በወይራ ዛፎች ድርቁን ስለመቋቋማቸው ነው የሚያነሱት፡፡