የግብጽ በአስር አመት ውስጥ አጋጥሟት የማያውቀው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷ ተነገረ

ግብጽ  በአሥር ዓመት ውስጥ አጋጥሟት በማያውቅ ኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ መግባቷ ተገለጸ

የሀገሪቱ መንግስት የተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉ ለግሽበቱ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡  

እኤአ በባለፈው ሀምሌ ወር ግብጽ በሁለት አምስት አመታት ውስጥ አይታው የማታውቀው የዋጋ ግሽበት አጋጥሟታል፡፡ የሃገሪቱ መንግስት ኢኮኖሚያዊ መሻሻል ለማምጣት በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ያደረገው የዋጋ ጭማሪ እንደምክንያት ተነስቷል፡፡

የሀገሪቱ ማዕከላዊ ስታስቲክስ መረጃ  ኤጀንሲ ባወጣው መረጃ መሠረት የዋጋ ግሽበቱ በሰኔ ወር ከነበረው 29 ነጥብ 8 በመቶ በአንድ ወር ውስጥ የ3 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 33 በመቶ ደርሷል፡፡

በዚህም መሠረት የዓመት አማካኝ የግሽበት መጠን ወደ 35 ነጥብ 26 በመቶ እንዳደገ የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ አስታውቋል፡፡   

ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ኃይል ላይ የዋጋ ንረት ተከስቷል፡፡ የግብጽን ኢኮኖሚ ለማሻሻልም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ የሀገሪቱን ገቢ እና ወጪ ለማመጣጠን እንዲሁም የመንግስትን የወጪ መጠን ለማስተካከል የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ ሃገሪቱ መስራት አለባት ብሏል፡፡ 

በግብጽ የኢኮኖሚ ጥናት ባለሙያ የሆነው ሬድዋን አልሰውፊ መንግስት የተለያዩ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት አለበት ብሏል፡፡

የግብጽ ማእከላዊ ባንክም በውጭ ምንዛሬዎች ላይ እና በሀገሪቱ መኖር ስላለበት የወለድ መጠን ላይ ለመወያየት በቀጣይ ሳምንት ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

አልሰወፊ ከጥናቱ በኋላ እንዳለው የመንግስት አካላት የተፈጠረውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለማረጋጋት በአገልግሎቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ እንዲያደርጉም አሳስቧል፡፡