በአንታርክቲካ የተደበቁ የእሳተ ገሞራዎች እንደሚገኙ ተመራማሪዎች ገለጹ

ከአንታርክቲካ ግግር በረዶዎች ጀርባ የተደበቁ ታላላቅ እሳተ ገሞራዎች እንደሚገኙ የኢድንበርግ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ገለጹ፡፡

እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ታላላቅ እሳተ ገሞራዎች ከአንታርክቲካ ግግር በረዶዎች በታች ተገኝተዋል፡፡

ጥናቱ እንዳመለከተው ከአንድ መቶ 138 እስከ 178 የሚደርሱና ከታች ሰፋ ብለው ከላይ ጠበብ ያሉ ህንጻ መሰል ግኝቶች ተስተውለዋል፡፡

በምዕራባዊው የአንታርክቲክ ስምጥ ሸለቆ የተገኙት እነኚህ ግኝቶች ምናልባትም ታላላቅ እሳተ-ገምራዎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ነው የተመለከተው፡፡

ከእነዚህ መካከል ዘጠና አንዱ እሳተ ገሞራ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን አነኚህ እሳተ ገሞራዎች እስከ አስራ ሁለት ሺህ ጫማ ወይም ሦስት ሺህ 850 ሜትር ርዝመት እንደሚኖራቸውም ታወቋል፡፡

ከእነዚህ እሳተ ገሞራዎች ኃይል ከፍተኛ ሲሆን አንዱ እሳተ-ገሞራ ብቻ 12 ሺህ 432 ስኩዌር ኪሎሜትሮችን ይሸፍናልም ተብሏል፡፡

ይህ ርቀት ከምስራቅ አፍሪካ እስከ ሰሜን ምዕራባዊ አሜሪካ ድረስ ያለውን ያህል ሲሆን በረዷማዋን አህጉር የአለም ትልቋ የእሳተ ገሞራ ቀጠና ያደርጋታል፡፡

ምንም እንኳ የእሳተ ገሞራዎቹ መገኘት ቢረጋገጥም ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ደረስ እነኚህ እሳተ ገሞራዎች የሚፈነዱ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ይፋ አልሆነም፡፡

ይሁን እንጂ እሳተ ገሞራዎቹ የአንታርክቲካ ግግር በረዶዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርሱ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

በሌላም በኩል የእሳተ ገሞራው መፈንዳት ግግር በረዶዎቹ ከቀለጡ በኋላ ዳግም በተረጋጋ ስፍራ ላይ እንዲቀመጡ ከማስቻል አንጻር ጠቄሜታ አለውም ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ከሌሎቹ በረዶዎች አንጻር ስስ በሆኑት የአይስላንድ ደሴት በደረሰው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የበረዶ ግግሮች መቅለጣቸውን ጥናቱ አያይዞ ጠቅሷል፡፡(ምንጭ: ሲጂቲኤን)