የዘንድሮ ዓመት የተመዘገበው የሙቀት መጠን እጅግ ከፍተኛው ነው ተባለ

በዘንድሮው አመት የተመዘገበው የሙቀት መጠን እስካሁን ከተመዘገበው እጅግ ከፍተኛው  ነው ተባለ፡፡

አለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ይፋ ባደረገው መረጃ እኤአ በ2017 ዓመት የተመዘገበው ሙቀት ክብሮሰን መሆኑን ገልጿል፡፡ ድርጅቱ በዓመቱ የኢል ሊኖ ክስተት ጎልቶ ባይታይም  የዓለም ሙቀት አይሏል ብሏል፡፡

የሳይንስ ሊቃውንት የሰው ልጅ እለት ተዕለት እንቅስቃሴ የአለም አየር ንብረት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ መሆኑን በተጋጋሚ ያወሳሉ፡፡ 

በዚህ ዓመት የታዩት ያልተለመዱ የአየር ሁኔታ ክስተቶችም  መንሴያቸው የሰው ልጅ ተፅዕኖ እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የዘንድሮው ዓመት የአየር ንብረት ምክክር የዓለም አቀፍ ሜትሮሎጂ ድርጅት ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡    

በአከባቢ አየር ውስጥ ያለው የግሪን ሃውስ ጋዝ ልቀት መጨመር በአየር ውስጥ ከፍተኛ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ተከማችቶ ለሙቀት መጨመር መንስኤ መሆኑን ባደርገው ጥናት አመላክቷል፡፡        

የአለም ሜትሮሎጂ ድርጅት ያከናወነው ጥናት እንደሚያሳየውም የምድራችን ሙቀት በአሁኑ ሰዓት ከ1ነጥብ 3 በመቶ በላይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በጥናቱ መሠረትም ከ 1950 ወዲህ አማካይ የሙቀት መጠን ጨምሮ ታይቷል፡፡ ውጤቱ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከ 1 ነጥብ 5 በላይ መድረሱን ተከትሎ በደሴቶች አካባቢ አደጋዉ ሊካፋ ይችላልና ተገቢ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ጥናቱ አሳስቧል፡፡

የጥናቱ ዝርዝር እንደሚያሳየው የ2017 ሙቀት ከ 1983 አስከ 2010 በ አማካይ በ 0ነጥብ 47 በመቶ  ጨምሯል፡፡  

ከ2016 ኤል ሊኖ ከተካሰተበት አንፃር ሲታይ ግን 0ነጥብ 56 አማካይ ቀንሶ ታይቷል፡፡

አለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ተቋም የዘንድሮው አመት በ2015 ከተመዘገበው ሙቀት ሁለተኛው አልያም ሶስተኛው ሊሆን እንደሚችል አስቀምጧል፡፡

ያለፉት ሶስት አመታት በተመዘገባበችው የሙቀት መጠን ቀዳሚውን ሶስት ደረጃ የሚይዙ ናቸው ሲሉ የተቋሙ ዋና ፀሓፊ ፔትሪስ ታላስ ይናገራሉ ፡፡

እስከ 50 ሴልሸስ እጅግ አዳጋች የሆነ የአየር ንብርት በኤስያ መከሰቱ በዚህ ዓመት ተመዝግቧል፡፡ ታይቶ የማይታወቅ የሀሪኬን፤የጉዳት መጠኑ እጅግ የሰፋ ጎርፍ ብሎም በካሪቢያን እና በአትላንቲክ በተከታታይ የተከሰቱ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ተከስቷል፡፡

አደጋው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን የጎዳ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ድርቅ ብሎም ጎርፍ በአፍሪካ ተከስቶ ነበር ሲሉም ፀሀፊው አክለዋል፡፡

የሳይንስ ሊቃውንት እኤአ በ2017 የተከሰተውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን አስመልክቶ ተጨባጭ ጥናት ማድረግ አለባቸው ሲሉም ምክራቸውን ያክላሉ፡፡

እየጨመረ የመጣው ያለም ሙቀት የባህር ማዕበል እንዲከሰትና ለጎርፍ መጥለቅለቅ መንስኤ  ሊሆን እንደሚችል የዘገባዉ ምንጭ ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

በተጨማሪም በሴራ ሊዮን፤ በኔፓል፤በሕንድ፤ በባንግላዴሽ እና በፔሩ መካከል  በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ውድመት አጋጥሞ  ነበር፡፡

በተቃራኒው ድርቅ እና ሙቀት በአብዛኛዎቹ  የአፍሪካ እና የደቡብ አሜሪካ አካባቢዎች ተፅእኖ አሳርፏል፡፡ በሶማሊያ ከግማሽ በላይ የሚሆን እርሻ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በሀገሪቱ ድርቅ ባሳደረው ተፅዕኖ ከብቶች ከ 40-60 በመቶ  እንዲቀንስ ምክኒያት ሆኗል፡፡በጥቅሉም በምስራቅ አፍሪካ ከ 11 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ጠምግብ እጥረት ተዳርገዋል፡፡

 እንደ የእንግሊዙ ሬዲንግ ዩነቨርሲቲ የአየር ንብረት ሳይንስ ፕሮፌሰር ሪቻርድ አላን 2017 በአየር ንብርት ለዉጥ አስከፊ ክስተቶች አልፈዉበታል፤ በሰበአዊ ሂዎት ላይ የደረሰዉ ጉዳትም በአጅጉ  ጨምሯል፡፡

የምድር ሙቀት መጠን  በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ  በፓሪስ የአየር  ስምምነት ሰነድ ባስቀመጠዉ የጋዝ ልቀት መስፈርት መመራት የግድ ይላል፡፡ ሲሉም ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብር ምክክር ጉዳዩን ትኩረት የሰጠዉ ሲሆን በፓሪስ ስምምነት አላማ መመራት ካልተቻለ የአለም ዜጎች ፈታኝ እጣፈንታ የጠብቃቸዋል ያሉት የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ፀሃፊ ፓትሪሺያ ኢስፓኖሳ ናቸዉ፡፡