ሱዳንን ከግጭት የፀዳች ለማድረግ እንደሚሠሩ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አስታወቁ

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽር  ሱዳንን በቀጣይ ሶስት አመታት ከግጭት የፀዳች እንደሚያደርጉ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አስታወቁ ፡፡

በሀገሪቱ መንግስት መሠረት ኦማር ሀሰን አል በሽር እ.ኤ.አ በ2020 የሥልጣን ዘመናቸው  እንደሚጠናቀቅም  ተገልጿል ፡፡

በምዕራብ ሱዳን የምትገኘው ዳርፉር አማፂዎች ከሀገሪቱ መንግስት ጋር የፈጠሩት አለመግባባት እና የተከተለው ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አል በሽርን ዛሬም በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እየተፈለጉ ይገኛል፡፡

ዳርፉር ላለፉት14 አመታት በሰብአዊ ቀውስ እየታመሰች ነው፡፡ ይህን ችግር ጨምሮ ሌሎች በሀገሪቱ ለሰላም እጦት የሆኑ ምክንያቶች በቀጣይ ሶስት አመታት እልባት እንዲያገኙ በማድረግ ሱዳን የሰላም ተምሳሌት ትሆናለች ብለዋል ፕሬዚዳንት አልበሽር፡፡

በፕሬዚዳንትነት መንበረ ሥልጣን የመቆየት እድላቸው ሶስት አመት ብቻ ነው፡፡ ህገመንግስቱ ለፕሬዝዳንቱ የሠጣቸው የስልጣን ዘመን ገደብ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2020 ያበቃል፡፡

ከፓርቲያቸው እና ከመንግስታቸው አስተዳደር ኦማር ሀሰን አል በሽር ዳግመኛ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው እንዲሳተፉ ህገ መንግስቱን የእናሻሽል ሩምሩምታ እየተሰማ ነው፡፡

የሱዳን ወጣቶች ህብረት ጠቅላላ ስብሰባን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሬዝዳንት አል በሽር በዳርፉር ያለው አመፅ ሊበቃው ይገባል ብለዋል ።  

አማጺዎች ወደ ሰላም እና ድርድር መድረክ እንዲመጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አማጺዎቹ ለድርድር እምቢተኛ ከሆኑ ደግሞ ሊታገሏቸው የሚገባው የሱዳን ወጣቶች ብቻ መሆናቸው ሊታወቅ እንደሚገባ ሌላው መልዕክታቸው ሆኗል፡፡ 

ኦማር ሀሰን አል በሽር እናንተ ወጣቶች ከቂም ጥላቻ የወጣች ሀገርን ብናስረክባችሁ እንወዳለን በማለት የዳርፉር  ሰላም እንዲመለስ  ይረዳል ያሉትን እቅድ ግሪን ዳርፉር በሚል ስያሜ ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህ የሰላም እቅድ ከኮርዶፋን፣ብሉ ናይል እና ዳርፉር ግጭቶቹን ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ ለመሸሽ በየስደተኛ ጣቢያ ያሉ ስደተኞች ወደቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ህይወት ዳግመኛ እንዲመሩ የሚያስችል መንገድ ተቀይሶበታል፡፡

ከስደት ተመላሾቹ መቋቋሚያ የሚሆናቸውን መሠረታዊ ቁሳቁስ ያገኛሉም ተብሏል፡፡አልበሽር የጦር መሳሪያ መያዝ ያለበት በመደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ብቻ እንደሆነ በግሪን ዳርፉር የሰላም እቅዳቸው በማስቀመጥ የጦር መሳሪያ በእጃቸው የሚገኝ የዳርፉር ነዋሪዎች ለመንግስት ማስረከብ አለባቸው ብለዋል፡፡.

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት የጦር መሳሪያ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር በሰላም ዙሪያ የሚደረግ ድርድር እንደሌለ በእቅዳቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

በተለይም እነዚህ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በሀገሪቱ ላይ የሚያደርሱትን ትንኮሳ ማቆም አለባቸው ሲሉም ተደምጧል፡፡

የሱዳን መከላከያ ኃይል ከሱዳን ህዝቦች ነጻነት ግንባር አማጺዎች ጋር በብሉ ናይል እና ደቡባዊ ኮርዶፋን ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ በጦርነት ላይ ሲሆን በዳርፉርም የታጠቁ ኃይሎች ከማዕከላዊ መንግስቱ ጋር መስማማት ከታሳናቸው 14 አመታት ተቆጥረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት አል በሽር  በመፈንቅለ መንግስት የያዙት ሥልጣን የፈረንጆቹ 2020 ላይ ሲደርስ ለ31 አመታት ሱዳንን የመሩ ግለሰብ ያደርጋቸዋል ሲል የዘገበው ሱዳን ትሪቡን ነው፡፡