በኢራንና ኢራቅ ድንበር በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ200 ሰዎች በላይ ህይወት መጥፋቱ ተገለጸ

በሰሜን ኢራን እና ኢራቅ ድንበር ላይ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ከ200 በላይ ሰዎች ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸው ተገለጸ ፡፡

የመሬት መነቀጥቀጡ በተያዘው ዓመት ትልቁ የተባለ ሲሆን ከ70 ሺህ በላይ ዜጎችን መጠለያ አልባ አድርጓቸዋል፡፡ አደጋው በአካባቢው ላይ የሚገኑ የቱርክ፣ እስራኤል፣ እና ኩዌትን ነክቷቸዋል፡፡

የአሜሪካው የጂኦሎጂካል ሰርቨይ ተቋም እንዳስታወቀው በሰሜን ኢራን እና ኢራቅ ድንበር አካባቢ ላይ የተከሰተው መሬት መንቅጥቀጥ የዓመቱ ከበድ ያለ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አደጋው በኢራን ግዛት በሆነው ደርባንዲክሃን እና በቅርቡ ከአይ ኤስ አይ ኤስ ነፃ የወጣችው የኢራቋ ግዛት ኩርድስታን ግዛት ተከሰተ ነው ተከሰተው፡፡

በሬክተር ስኬል 7ነጥብ 3 ሬክትር የተመዘገበው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ200 በላይ ዜጎችን ሕይወት ሲቀጥፍ ከ2ሺህ 800 በላይ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከ70 ሺህ በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ካለመጠለያ አስቀርቷቸዋል፡፡

በጉዳቱ ህይወታቸውን ካጡት ውስጥ ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት ኢራናውያን መሆኑን ያስታዋሰው ዘገባው ኢስራኤለ፤ ቱርክ እና ኩዊትን በጥቁቱ አግኝቷቸዋል፡፡  አደጋው እኩለ ለሊት 6 ሰዓት ከ20 ገደማ ላይ  መፈጠር መቻሉ ከፋ እንዲሆን ያደረገው ሲሆን የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊቸምር እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

በኢራን የሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው በአደጋው በትንሹ ከስምንት ያላነሱ መንድሮች ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸው ናቸው፡፡

ሌሎች ደግሞ ምንም አይነት የኤሌክትሪክ እና ውሃ እጥረት ገጥሟቸዋል፡፡ በአካባቢው ላይ አደጋው ያስከተለው የመሬት መንሸራተት ደግሞ የእርዳታ ስራውን እያሰተጓገለው እንደሚገኝም ነው የተገለፀው፡፡

በአካባቢው ላይ ከሚኖሩት ውስጥ ከ2500 በላይ ኢራናዊያን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ለእነዚህም ዜጎች ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመውስድ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ቢሆንም በኢራንዋ ግዛት በሆነችው እና የአደጋ ከፍተኛ ሰለባ የሆነችው ሳርፖሌ የሚገኘው ሆስፒታል ለጉዳቱ ተጋለጠ በመሆኑ አገልግሎት መስጠት አልቻለም፡፡

አካባቢው በተፈጥሮው ዳገታማ ሲሆን በአካባቢው ላይ የተገነቡት ህንፃዎች ደግሞ በሽክላ ጡብ የተገነቡ በመሆናቸው በቀላሉ አደጋውን መቋቋም አልቻሉም፡፡ አሁን ከተሞቹ እንዳልነበሩ ሆነዋል፡፤ በኣካቢበው ላይ የሚገኙ ከ70 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆነዋል፡፡

በኢራቅ በኩል እስካሁን ከ321 በላይ የሚሆኑ በኩርዲሽ ግዛት የሚኖሩ ዜጎች የጉዳቱ ሰለባ ናቸው፡፡ የኢራቅ ከተማ የሆነችውን ባግዳድን የገፈቱ ቀማሽ ስትሆን በዚህች ከተማ ሰባት ሰዎች ህይታቸው አልፏል፡፡