በሰሜን አሜሪካ 7ነጥብ 6 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የርዕደ መሬት አደጋ ተከሰተ

 በትናንትናው ዕለት በመካከለኛውና ሰሜን አሜሪካ 7ነጥብ6 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ ከፍተኛ  የርዕደ መሬት አደጋ ተከሰተ፡፡

7 ነጥብ 6 ሬክትር ሰኬል የተመዘገበው ርዕደ መሬት በቀጣይ የሱናሚ አደጋ ስለመምጣጡ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች  እየተናገሩ ይገኛሉ ፡፡

በርዕደ መሬቱ እስካሁን የአሜሪካዋ ሁንዳራስ ከተማ የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ቨርጂኒያ ደሴት ተመተዋል፡፡  

አደጋውን በተመለከተ የአሜሪካው የሱናሚ ማዕከል በርዕደ መሬቱ የተጉዱ ከተሞች አሁንም ህልውናቸው አደጋ ውስጥ ነው ሲል አስታውቋል፡፡

ትላንት ከካሪቢያን ባህር አካባቢ እንደተነሳ የተነገረለት ከባድ ርዕደ መሬት በአካባቢው ላይ የሚገኙ ከተሞችን ህልውና አደጋ ውስጥ እንደከተታቸው ነው የአሜሪካው የሱናሚ ማዕከል ያስታወቀው ፡፡

7 ነጥብ 6 ሬክተር ስኬል የተመዘገበው የርዕደ መሬት አደጋው  እስከ 519 ኪሎሜትር ድረስ በመጓዝ በአካባቢ ላይ ያሉ ከተሞችን ሊመታ መቻሉ ተመልክቷል ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የርዕደ መሬቱ መከሰት በድጋሚ የሱናሚ አደጋ መምጫ ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

በእነዚህ ከተሞች ላይ አደጋ ስለመድረሱ እንጂ ተለይቶ የተመዘገበ አደጋ አለመኖሩን የወጡት ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡

በተለይ አደጋው ከተነሳበት አካባቢ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙት የአሜሪካዋ ሁንድራስ እና ቤሊዝ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ስለመሆናቸው እየተነገረ ነው ፡፡                       

በከተሞቹ ውስጥ አሁን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በአደጋው ስጋት ምክንያት ከቤት እየለቀቁ ያሉ ነዋሪዎችን የማረጋጋት ሥራ ብቻ እየሰሩ ስለመሆናቸው እና ስለደረሱ አደጋዎች ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ስለማድረጋቸው እና ለቀጣይ እርምጃ እየተጠባበቁ መሆናቸዉን ዘ ጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል፡፡

የተከሰተውን ርዕደ መሬት አስመልክቶ ጥናት እያደረገ እና ሪፖርቶችን ይፋ እያደረገው ያለው የአሜሪካው የስነ ምህዳር ጥናት ተቋም ግን ርዕድ መሬቱ 7 ነጥብ 8 ሬክትር ስኬል የተመዘገበ ሲሆን ከ 600 በላይ ኪሎሜትሮችን ሊያዳርስ ችሏል ነው እያለ ያለው፡፡ 

እንደ የስነ ምህዳሩ ተቋም ሪፖርት እንደሚያሳየው የርዕድ መሬቱ  እስከ 10 ኪሎሜትር ጥልቀት ያለው ሲሆን በድጋሚ የሱናሚ አደጋ ሊከስት ስለመሆኑ ማሳያ ሊሆን ይችላልም ብሏል፡፡

እስካሁን በከተሞቹ ላይ የደረሰ አደጋ ባይመዘገብም ርዕድ መሬቱ ያለው ክብደት ከፍተኛ በመሆኑ አደጋው እስካሁን የነካቸው ከተሞች በንቃት ሊጠባበቁ እንደሚገባ ተቋሙ አስጠንቅቋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሁለት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች  እኤአ በ2018 ከአምስት ያላነሱ ከወትሮ ከበድ ያሉ ርዕደ መሬቶችን አለማችን ሊታስተናግድ ትችላለች ብሎ መተንበዩ የሚታወስ ሲሆን የዚህም አንዱ አካል ሊሆን ይችላል ነው እየተባለ ያለው፡፡( ምንጭ: ዘጋርዲያን)