በኢንዶኔዥያ በተከሰተው የእሳተጎሞራ ፍንዳታ እና ሱናሚ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

በኢንዶኔዥያ  በተከሰተው የእሳተጎሞራ ፍንዳታና ሱናሚ  ጉዳይ የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥር እያደገ መምጣቱ  ተገለጸ  ።

በአደጋው  ምክንያት የሙዋቾች ቁጥር 281 ሲድርስ ጉዳት የደረሰባቸው ከ 1 ሺ በላይ መደረሱ ተገልጿል ፡፡

በኢንዶኔዢያ የባህር ዳርቻ ላይ ከ24 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው  የቅዳሜው  ሱናሚ በድንገት በመከሰት በሰው ይህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ  ከ700 በላይ ሕንፃዎችን ትንንሽ ሱቆች፤ ቤቶች ፤ ቪላዎች እና ሆቴሎች  ጠራርጎ ወስዱዋቸዋል ፡፡

የኢንዶኔዥያ ወታደሮች እና የህይወት አድን  ቡድኖች ለወራቶች ያህል ሲከሰት የነበረውን ከታታይ የእሳታ ጎመራ  ፍንዳታዎችን ተከትሎ በተፈጠረው  የመሬት መንሸራተት እና  ሱናሜ  ሳቢያ በባህር ዳርቻዎቹ ላይ በተከሰተው ከፍተኛ የአፈር ደልል ውስጥ በህይወት የተረፉ ሰዎችን የመፈለግ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሉዋል ፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት በአናክ ክራካቱ ቅዳሜ  አመሻሹ ላይ በተከሰተው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታ የመሬት መንሸራተት በባህር ዳርቻዎቹ ላይም ከፍተኛ ጉዳትን በማድረስ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ግዜ ድረስ  281 ሰዎችን ለሞት እንደዳረጋቸው እና ከ 1ሺ በላይ ሰዎችን ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል ፡፡

የህይወት አድን ሰራተኞች ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች እና በጎ ፈቃደኞች  በጋር ሆነው  ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት በምዕራብ ጠረፍ የጃቫ ደሴት ላይም ከፍተኛ ማሽኖችን በመጠቀም እን በሰው ሀይል በመታገዝ  ተጎጂዎችን እየፈለጉ ይገኛሉ።    

በዚህ የተፈጥሮ አደጋም ከ 1ሺ  በላይ ሰዎች  ጉዳት ሲደርስባቸው  ወደ 12 ሺ  የሚጠጉ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፍናቅለው ወደ ከፍታማ  ቦታዎች እንዲሄዱም ሆነዋል ፡፡

 የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ  አደጋው የተከሰተበትን አካባቢ  በመጎብኘት የመንግስት ባላስልጣናቱ ለአደጋው የሰጡትን አፋጣኝ ምላሽ እና የህየወት እድን ስራው ተካፋይ በጎፍቃደኞችን  ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል፡፡

የህክምና ቁሳቁሶችም የጦር ኃይሉ ቡድን በተለያዩ ገጠሮች ላይ የሚገኙትን በመጠቀም የማከፋፈል ስራዎችም በመከናውን ላይ ነው ፡፡(ምንጭ: ሮይተርስ)