በብራዚል አንድ የብረት ማዕድን ማውጫ ግድብ ተደርምሶ ዘጠኝ ሰራተኞች ሲሞቱ 300 ያህሉ የገቡበት አልታወቀም ተባለ

በብራዚል አንድ የብረት ማዕድን ማውጫ ግድብ ተደርምሶ ዘጠኝ ሰራተኞች ሲሞቱ 300 ያህሉ የገቡበት አልታወቀም ተባለ፡፡

ባለፈው አርብ ዕለት ግድቡ የተደረመሰው በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ሲሆን ያደረሰው ጉዳት ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

በቅርቡ የተደረገውን የብራዚል ምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ አደጋው ወደ ደረሰበት ስፍራ ለማቅናት በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

በጉዳቱም ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸውና መንግስታቸው የአደጋውን መንስኤ እንደሚያጤን አስታውቀዋል፡፡

በጨለማ የደረሰውን ይህንን አደጋ ተከትሎ የጠፉ ዜጎችንና የሟቾችን አስክሬን ለመፈለግ የድንገተኛ ቡድን ተቋቁሞ ወደ ስፍራው አቅንቷል ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ ዜና አውታሮች ግድቡ በሚሊዮን ቶን የሚገመት ውሃ አቁሮ አንደበር ጠቁመዋል፡፡ (ምንጭ፡-አልጀዚራ)