350 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

መጋቢት 27/2013 (ዋልታ) – 350 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡