409 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

ግንቦት 25/2013 (ዋልታ) – 409 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።