በጅማ ከተማ ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 75 ባለሃብቶች ፈቃድ ወሰዱ

በጅማ ከተማ ከ98 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 75 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደው ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸውን የጅማ ከተማ ኢንቨስትመንት ጽህፈትቤት ገለፀ፡፡

በጅማ ከተማ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ98 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 75 ባለሃብቶች ፍቃድ ወስደው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ መሠማራታቸውን የጅማ ከተማ ኢንቨስትመንት ምክትል ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሐሰን ገልጸዋል፡፡

በጅማ ከተማ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወስደዉ ወደ ሥራ የገቡ ባለሃብቶች  የጅማ ከተማን የልማት እንቅስቃሴና የራሳቸውን አላማ ለማሳካት የድርሻቸውን ለመወጣት በፍጥነት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት አመታት በከተማዋ ወደ ሥራ የገቡ ባለሃብቶች ግንባታቸውን አጠናቀው ለአከባቢው የተለያዩ አገልግሎቶችን በመሥጠት የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ቢሆንም የከተማውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማሳደግ በመንግስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰጠዉ የአገልግሎት መሻሻል እንዳለበት ነው የገለፁት፡፡

የጅማ ከተማ የኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሱልጣን ሐሰን ከባለሀብቶቹ የተነሱ ሓሳቦች ትክክል መሆኑን አንስተዉ፥ ችግሮቹ አሁን እንደተፈቱና መንግስት የኢንቨስትመንት ሥራ እንቅስቃሴ በይበልጥ ለማቀላጠፍ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጅማ ከተማ በአንደኛዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን 136 ሚሊየን ካፒታል ያስመዘገቡ 81 ባለሃብቶች ወደ ሥራ በመግባት ለ 19 ሺህ  ዜጎች የሥራ እድልን እንደፈጠሩ  ተገልጿል፡፡