ኢትዮቴሌኮም ለደንበኞቹ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ነፃ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ኢትዮቴሌኮም ለደንበኞቹ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ነፃ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

አገልግሎቱ ዛሬ የሚጀምረውን አዲስ የበጀት ዓመት አስመልክቶ ለደንበኞቹ ያቀረበው ስጦታ መሆኑን አስታውቋል።

አዲሱን በጀት አመት አስመልክቶም ለሁሉም የኢትዮ – ቴሌኮም ደንበኞች 20 ደቂቃ የሀገር ውስጥ የድምጽ ጥሪ እና 30 የሀገር ውስጥ አጭር የጽሑፍ መልዕክት እንዲያገኙ ይደረጋል።

ከዚህ ባለፈም 1 ጊጋ ባይት የኢንተርኔት አገልግሎት በነፃ ያገኛሉም ነው የተባለው።

የነፃ አገልግሎቱ ከዛሬ ሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 3 ቀን የሚቆይ ነው ተብሏል።