የኢንሱሊን መርፌን ይተካል ተብሎ የታመነበት እንክብል ውጤታማ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26/2008(ዋኢማ)-የስኳር ህመም ተጠቂዎች በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን ጉልኮስ መጠን ለማስተካከል ኢንሱሊን በመርፌ መልክ በየእለቱ እንደሚወስዱ ይታወቃል።

ከሰሞኑ የተሰማው አዲስ የጥናት ውጤት ደምጎ መርፌውን ሊያስቀር ይችላል ነው የተባለው።

ይህም በመርፌ መልክ የሚሰጠውን የኢንሱሊን ህክምና በእንክብል የሚቀይር ሲሆን፥ እንክብሉም በሙከራ ደረጃ ውጤታ መሆኑ ነው የተጠቆመው።

እንክብሎቹ የኖቤል ሽልማት አሸናፊ በሆኑት ተመራማሪዎች ድጋፍ የተሰራ መሆኑም ነውየተነገረው።

በአሁኑ ጊዜም የኢንሱሊን እንክብሉ ሙከራ ሶስተኛ መእራፍ ላይ የደረሰ ሲሆን፥ ይህም መድሃኒቱ ተማሚዎች ዝንድ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ ለማግኘት የሚያስችል ምእራፍ ነው ተብሏል።

“ሆሊ ግሬይል ኦፍ ዲያቤትስ ሪሰርች” የተባለ ድርጅ እንዳስታወቀው፥ የኢንሱሊን እንክብሎቹን መስራት ያስፈለገው በአሁኑ ጊዜ በርካታ ሰዎች ያለ ፍላጎታቸው የስኳር መጠናቸውን ለመቆጣጠር በሚል ራሳቸውን መርፌ ሲወጉ ይስተዋላል፤ ይህንን ለማስቀረት እና ሰዎች በፈለጉት አማራጭ ህክምናውን እንዲያገኙ በማሰብ ነው ተብሏል።

ለዚህ ይረዳል ተብሎ የታመነበት እንክብል ከሁለት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ታካሚዎች ዘንድ እንደሚደርስም ተቋሙ አስታውቋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)