ዲያስፖራዎቹ በአገሪቱ ልማት ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

ኮምቦልቻ፤ ሐምሌ 19/2008(ዋኢማ)- 2ኛውን የኢትዮጵያን  የዲያስፖራ  ቀንን  ለማክበር   ከተለያዩ  የዓለም  አገራት  የመጡ  ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  በአገሪቱ  ሁለንተናዊ  የልማት  እንቅስቃሴ ላይ  ለመሳተፍ   ከመቼውም ጊዜ  በላይ ዝግጁ መሆናቸውን  ገለጹ ።

የዲያስፖራ በዓልን  ለማክበር   ወደ  ባህርዳር  ከተማ  በመጓዝ  ላይ  የሚገኙና  ከተለያዩ   ውጭ  አገራት የመጡ  የዲያስፖራ  አባላት  ለዋኢማ  እንደገለጹት   የኢትዮጵያን  ተጨባጭ የዕድገት  ግስጋሴ   በአካል ተገኝተው  በማየታቸው  ደስተኛ እንደሆኑንና  በእውቀት ፣ ክህሎት ፣በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፎች  መዋለ ነዋያቸውን  በማፍሰስ  የትውልድ  አገራቸውን  ህዳሴ  ለማረጋገጥ የድርሻቸውን  እንደሚወጡ ተናግረዋል ።

የዲያስፖራ አባላቱ  ከአዲስ አበበባ  ተነስተው  ወደ  ባህርዳር ከተማ  በሚያቀናው ጉዟቸው የቻይናውን ኤቨር ፕራይዝ ፕላስቲክ  ፋብሪካ ፣ የሐበሻ ቢራ ፣ የዳሽን ቢራና የደብረ ብርሃን  እንጨት  ማቀነባባሪያ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል ።

ዋኢማ ያነጋገራቸው በእንግሊዝ ለ46 ዓመት የኖሩት ወይዘሮ ዘሪቱ ባይጨክን እንደገለጹት  በአገሪቱ የዲያስፖራ ቀን መከበር የአገሪቱ  የዲያስፖራ  አባላት  እርስ በእርስ ሓሳብ እንዲለዋወጡ እድል መፍጠሩንና በትውልድ አገራቸው በእንስሳት ሃብት ልማት ለመሠማራት  እየተዘጋጁ  መሆኑን ተናግረዋል ።

ሌላው ከአሜሪካ  የመጡት  ዲያስፖራ አቶ አለማየሁ አማረ በበኩላቸው በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ  መዋለ ነዋያቸውን በማፍሰስ  አገሪቱ    ወደ ኢንዱስትሪ  መር ኢኮኖሚ  ለመሸጋጋር ያስቀመጠችውን እቅድ ተግባራዊ ለማድርግ ረገድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል ።

በአገሪቱ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማስቀጠል ፈጣን አገልገሎትን  በመሥጠትና መልካም  አስተዳደርን ይበልጥ በማጠናከር  መንግሥት  የዲያስፖራ አባላት በአገር ውስጥ  ልማት ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ  በማሳደግ በኩል የበኩሉን ሚና መጫወት እንደሚገባው አቶ አለማየሁ  አስተያያታቸውን ሠጥተዋል ።

በአገር  አቀፍ ደረጃ  ከሓምሌ 25  እስከ 26 ድረስ ለሚከበረው   የዲያስፖራ  ቀን በዓልን ለማክበር    ከተለያዩ   የዓለም ክፍሎች   የመጡ  ኢትዮጵያውያን  ዲያስፖራ  አባላት  በሁለት  ቡድን ተከፋፈለው  በምስራቅና  በምዕራብ  አማራ ክልል  ጉብኝት እያካሄዱ ሲሆን  ከአካባቢው ማህበረስብ ደማቅ አቀባባል እየተደረገላቸው መሆኑን ዋልታ  እንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ።            