ኤርትራ ሄደዉ የነበሩት ሀኪሞች አገልግሎታቸውን ጨርሰው ተመልሰዋል

ወደ ኤርትራ በመሄድ ለሁለት ወር ነፃ የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ሀኪሞች አገልግሎታቸውን ጨርሰው ተመልሰዋል፡፡

ከባህርዳር ዩንቨርሲቲ እንደተመረቁ ወደ ኤርትራ በመሄድ ለሁለት ወር ነፃ የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ሀኪሞች አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸዉን ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም በአቀባበል ስርአቱ ላይ በድንገት በመገኘት ሀኪሞቹን ማመስገናቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶክተር አሚር አማን በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ገልጿል።