ሳምሰንግ በትርፍ ተንበሸበሸ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ23/2008(ዋኢማ)-ግዙፉ የደቡብ ኮሪያ ሳምሰንግ ኩባንያ ከባለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ የሞባይል ሽያጭ ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ፡፡

ኩባንያው በሁለተኛው ሩብ ዓመት የሞባይል ሽያጭ ትርፉ በ18 በመቶ ጨምሮ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ችሏል፡፡ ይህም በኩባንያው ታክ ከፍተኛ ትርፍ የተገኘበት ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ለትርፉ ማደግ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ ሰቨን( Galaxy S7) እ4ና ጋላክሲ ኤስ ሰቨን ኤጅ( Galaxy S7 Edge) የተሰኙት ስማርት ስልኮች ተፈላጊነታቸው በጣም መጨመሩ በምክንያነት ተገልጿል፡፡

በስማርት ስልኮችና በታብሌት ምርቶቹ በቀጣይም በገበያ ውስጥ ተፈላጊነቱ እንደሚጨምር ገልፆ፤ከሌሎች መሰል ምርት አቅራቢና አምራች ድርጅቶች የተሻለ ሆኖ ለመቀጠል አቅዷል፡፡

በሞባይል ዘርፍ ኩባንያው በየዓመቱ እየተሻሻለ መሆኑም በመረጃው ተመልክቷል፡፡ በዚህ ዘርፍም በየዓመቱ 57 በመቶ የትርፍ ዕድገት እያስመዘገበ መምጣት ችሏል፡፡ በመሆኑም ከሞባይል ስልኮች ብቻ ከሶስት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ትርፍ አግኝቷል፡፡

በሶስተኛው ሩብ ዓመት ያሰራጨው ባለትልቅ ስክሪን ውድ ስማርት ስልክ በስማርት ስልክ ዘርፍ ሪከርዱን ይሰብራል የሚል እምነት አለው ኩባንያው፡፡

ከአሜሪካው አፕል ኩባንያ የተሻለ ሆኖ መገኘቱን ሳምሰንግ አስታውቋል፡፡ ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ድረስ ትርፉ 15 በመቶ መቀነሱን አፕል አስታውቋል፡፡ ይህ በቀጣይ ጊዜያት ትርፉ ላይም ጥላ እንዳያጠላ ተሰግቷል፡፡

የደቡብ ኮሪያው ግዝፉ ኩባንያ ሳምሰንግ ምርት የሆኑት ቴሌቭዥን፣ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣የአየር ማቀዝቀዣና ሌሎች ምርቶችም በገበያው በጣም ተፈላጊ እየሆኑ ነው፡፡ ተፈላነታቸውን በመጨመር ትርፋማነቱን በማሳደግ ለመቀጠል እንደሚሰራ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

ምንጭ፤ ቢቢሲ