ፊትን በማሳየት ብቻ መገበያያት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ

ፊትን በማሳየት ብቻ  መገበያያት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ

ቴክኖሎጂው እድሜን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚሰራም ከወደ እንግሊዝ የተሰማው ዘገባ ያመላክታል፡፡

በየግዜው  የሚፈበረኩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰው ልጅን ህይወት ቀለል በማድረግ ድርሻቸው የጎላ ነዉ፡፡

እንዳንዱን እንቅስቃሴን ቀለል በማድረግ እንዲሁም ግዜን ከመቆጠብ አኳያ አሁን የተሰራው የቴክኖሎጂ ውጤትም ደንበኞችን እፎይ አስብሏል፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ በየትኛውም ሰአት እና ቦታ ምንም አይነት ተንቀሳቃሽ የሂሳብ ካርድ ሳያስፈልግዎት ወደ መተግበሪያው ፊትዎን ጠጋ አድርገዉ በማሳየት ብቻ በአቅራቢያዎ ካለዉ ሱፐርማርኬት መገበያየት ያስችሎታል እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ፡፡

ታድያ እንዴት በእጅዎ የሚያሳዩት ገንዘብ አልያም ተንቀሳቃሽ የሂሳብ ካርድ ሳይኖር ይህንን አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ብለዉ ግራ መጋባትዎም አይቀርም፡፡

ይህ ፊትን በማሳየት ብቻ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለዉ ቴክኖሎጂ ቶቲ በተሰኘዉ የእንግሊዝ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰራ መተግበሪያ ሲሆን

ደንበኞች አልያም ተገልጋዮች ፎቶአቸዉን እና መንጃ ፍቃድ እንዲሁም ፓስፖርት አልያም መታወቂያቸን በስማርት ስልኮቻቸዉ ላይ በመጫን  ነዉ አገልግሎት ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡

ይህ መተግበሪያ ለየት የሚያደርገው ደንበኞች ማንኛዉንም ቁሳቁስ ለመሸመት በመተግበሪያው ላይ ቀድመዉ በሚያስቀምጡት የእድሜ ገደብ መሰረት ግብይት እንዲፈፅሙ በማድረግ መቆጣጠር ያስችላል፡፡

ለምሳሌ እድሜአቸው ያልደረሰ ማንናዉም ደንበኛ አልኮል ነክ ምርቶችን መፈፀም ቢፈልግ እንኳን መተግበሪያው ይህንን አያስችለውም፡፡

ዮቲ የተሰኘውን መተግበሪያ የፈጠራ ባለቤት ከሆኑት አንዱ የሆኑት ሮቢን ቶምብስ በበኩላቸው በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ላይ ይህ መተግበሪያ በሁለት ግዙፍ ሱፐርማርኬቶች ላይ ሙከራዉን ይጀምራል ብለዋል፡፡

ትክክለኛ  እና ታማኝ የሆነ መተግበሪያ በመፍጠር  ሰዎች በቀላሉ የሚፈልጉትን አገልግሎት በዚህ ቀላል በሆነ መተግበሪያ መስጠት የኩባንያዉ ዋነኛ አላማ እንደሆነም ነው በመረጃው የተገለፀዉ፡፡

ይህ መተግበሪያ በየትኛዉም ቦታ ምናልባም መታወቂያዎን አልያም የካርድ ሂሳብዎን ረስተዉ አንኳን ቢሄዱ ስልክዎ ላይ በተጫነዉ መተግበሪያ በቀላሉ የፊት ፎቶዎን በራስዎ ስልክ ላይ በማንሳት ግብይት መፈፀም ያስችልዎታል፡፡

እስከአሁን ባለዉ መረጃ መሰረት ከአንድ መቶ ሺ በላይ ተጠቃሚዎች ይህንን  ዮቲ የተሰኘዉን መተግበሪያ ለመጠቀም ፍቃድ መዉሰዳቸዉ ታዉቋል፡፡

ይህ ደግሞ አዲሱ ቴክኖሎጂ ምን ያህል ሰዎች በቃሉ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የሚያደርግ በመሆኑ የሰዎቹ ፍላጎትም በዚሁ ልክ እጨመረ መምጣቱን ያሳያል ተብሏል፡፡