ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከኳታር ቢዝነስ ኮሚኒቲ ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኳታር የቢዝነስ ኮሚኒቲ ጋር ውይይት አደረጉ ፡፡  

ኢትዮጵያ ለኳታር ባለሃብቶች፣ የቢዝነስ መዳረሻ አቅም ሊሆን የሚያስችላት የተመቻቸ ሁኔታ እንዳላት ገልጸዋል፡፡  ጠቅላይ ሚንስትር  ኃይለማርያም  በተጨማሪም ኢትዮጵያና ኳታር  በተለያዩ  ዘርፎች  በጋር  በመሥራት  በአንድነት ማደግ ይችላሉ  ብለዋል፡፡

የኳታር ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ኢትዮጲያ ዝግጁ መሆኗን ገልጸው፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ይዘው ዱሃ ድረስ መምጣታቸው ለዚህ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ብዙ ቁጥር ያለው ህዝብ፣ ሰፊ ገበያ፣ የተመቻቸ የመልካ ምድር አቀማመጥ፣ መልካም የአየር ሁኔታ እንዲሁም በቀላሉ ሊሰለጥን የሚችል ወጣት የሰው ኃይል ያላት በመሆኗ ባለሃብቶቹ በቱሪዝም፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በኢነርጂ፣ በግብርናና በሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩ ጋብዘዋል፡፡

ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ መስኮች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡