ፌስቡክ ሰዓት መቆጣጠር የሚያስችል መተግበሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው

ፌስቡክ ሰዓት መቆጣጠር የሚያስችል መተግበሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ እነድሆነ ተገልጸዋል፡፡

መተግበሪያው በተለይ ታዳጊዎች በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ለማሳወቅ ያስችላል ተብሏል፡፡

እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2004 በወጣቱ ማርክ ዙክን በርግ የተመሰረተው የማህበራዊ ትስስር መፍጠሪያ ገጽ ፌስቡክ በዓለም ዙሪያ በርካታ ሰዎች ከሚጠቀሙባቸው ማህበራዊ የትስስር ገጾች ውስጥ ቀዳሚው ነው፡፡

የትስስር ገጹ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ገደማ ተጠቃሚዎች እንዳሉትና እነዝህም ተጠቃሚዎች በወር ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ የሚጠቀሙ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ከተመሰረት 13 አመታትን ያስቆጠረው የዚህ የትስርሰር ገጽ ተጠቃሚዎች ቁጥርም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መቷል፡፡

ፌስቡክ ከሌሎቹ ማህበራዊ ድህረ ገፆች በተሻለ ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑ እና በተለያዩ ቋንቋዎች መጠቀም ማስቻሉ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከፍተኛ እንዲሆን እንደረዳው ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ልክ እንደ ተጠቃሚዎች ቁጥር ገጹ አዳዲስ ማሻሻያ ይዞ ብቅ እንደሚል ይታወቃል፡፡

ፌብቡክ በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ወር ውስጥ አንድ ቢሊየን ተጠቃሚዎች እና 10 ሚሊየን ሰዎች የጎበኙት ብቸኛው ማህበራዊ የትስስር ገጽ ሆኖም ተመዝግቧል፡፡

በርካታ ተጠቃሚዎች ብዙ ጊዚያቸውን በተለይ ወጣቶች የሚያጠፉበት ይህ ማህበራዊ ድህረ-ገፅ መረጃን ከመጠበቅ፣ ከሰነ ልቦና ተፅዕኖና በተለያዩ ሀጋራት ባህሎች እና ወግ የማይፈቀዱ ድርጊቶችን እና ሁኔታዎች በማሰተናገዱ ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡

በተለይም እድሜያቸው ከ12 እሰከ 18 ዓመት ያሉ ታዳጊዎች አብዛኛውን ጊዜያቸውን በእንቶ ፈንቶ እንዲያሳልፉ ምክኒያት ከሚሆኑ ማህበራዊ ድህረ ገፆች ፌስቡክ ቀዳሚው ነው፡፡

ይህን እና ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለማፍታት በማሰብ ፌስቡክ ከሰሞኑ የታዳጊዎችን ሰዓት አጠቃቀም ሊያሻሽል የሚያስችል መተግበሪያ አገልግሎት ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

ይህ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ማህበራዊ ድህረ ገፆች ላይ እየተጠቀሙ የሚቆዩበትን ጊዜ ማሳወቅ የሚያስችል ሲሆን ማንኛውም ፌስቡክን የሚጠቀም ሰው የሚጠቀምበትን ጊዜ በራሱ መወሰን እና ገደብ ማስቀመጥ የሚችልበት ነው፡፡

75 በመቶ ሚሆኑት የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የፌስብክ ገፃቸውን በየ15 ደቂቃ ልዩነት ይጎበኙታል፡፡ ይህ ደግሞ ምንም አይነት የጊዜ ገደብ ባለመኖሩ የተፈጠረ መሆኑ እና ለዚህ ችግር ደግሞ ይህ መተግበሪያ እንደ አማራጭ ያገለግላል ሲል ዘቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡